ዜና፡ በትግራይ ክልል የሚገኙ ብፁዓን አባቶች ባካሄዱት የኤፒስ ቆጶሳት ሹመት ዙሪያ ለመምከር ሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18/2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በትግራይ ክልል የሚገኙ ብፁዓን አባቶች ባካሄዱት የኤፒስ ቆጶሳት ሹመት ዙሪያ ለመምከር ለቀጣይ ሳምንት አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ተገለጸ። ሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባውን የጠራው በትግራይ ክልል የሚገኙ አባቶች መንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ብለው በማቋቋም በአክሱም የሰጡትን የኤፒስ ቆጶሳት ሹመት አስመልክቶ ውሳኔ ለማሳለፍ መሆኑን ሲኖዶሱ በሰጠው መግለጫ ጠቁሟል። በትግራይ ክልል የሚገኙ ብፁዓን አባቶች ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ተብለው በሚጠሩበት በማዕከላዊ ትግራይ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 15 እና 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ሹመት መስጠታቸውን ኮንኗል።

በመሆኑም የተከሰተው የዶግማ፣ የቀኖና እና አስተዳደራዊ ጥሰት አስመልክቶ ተወያይቶ ተገቢውን ለመወሰን ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪ ተላልፏል ብሏል፡፡

በየደረጃ ያሉ የቤተ ክርስቲያኗ የሥራ ኃላፊዎች እና ሊቃውንት እንዲሁም ምዕመናን ከቤተ ክርስቲያኗ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ እናስተላልፏል፡፡ የእምነቱ ተከታዮች የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ ተገቢውን ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ በትግዕስት እንዲጠብቁ አሳስቧል።

በትግራይ ክልል የተካሄደውን የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያላከበረና የቤተ ክርስቲያንን ማዕከላዊነት የሚጥስ በመሆኑ እንዲቆም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ መጠየቁን መዘገባችን ይታወሳል። ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የጳጳሳቱን ሹመት እንዲያስቆሙ ብሎም ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ ችግሮቹ በውይይት እንዲፈቱ መንግሥታዊ እገዛ በማድረግ የውይይት መድረክ እንዲያመቻቹልን ሲሉ መጠየቃቸውም ተካቷል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ እና በትግራይ ክልል በሚገኙ የእምነቱ አባቶች በመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መካከል የተፈጠረው ልዩነት ባልተፈታበት ሁኔታ የትግራይ አባቶች በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ሐምሌ 16 ቀን 2015 ዓ.ም በአክሱም ጽዮን የአዳዲስ ጳጳሳት ሹመት ማካሄዳቸው መዘገቡ ይታወሳል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.