ዜና፡ ኮካ ኮላ ለ30 የፕላስቲክ መሰብሰቢያ ማዕከላት እስከ 10 ሚሊየን ብር የሚደርስ ድጎማ እንደሚያደርግ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17/2015 ዓ.ም፡- የኮካ ኮላ መጠጦች አፍሪካ ከ30 የፕላስቲክ መሰብሰቢያ ማዕከላት ጋር የመሰብሰብ አቅማቸውን ለማሳደግ እንዲረዳ እስከ 10 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ድጎማ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራመ።

በሁለት ምዕራፎች ለአንድ አመት ተግባራዊ ሊደረግ በተቀመጠው የሙከራ ፕሮጀክት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለሚሰበሰብ 1,000 ኪ.ግ ፕላስቲክ 1,000 ብር ለመደጎም አቅዷል።

የዓለማችንን የማሸጊያ ችግር ያለፈ ታሪክ ለማድረግ በምድራችን ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ቁርጠኛ ነን። ይህ መልሶ ጥቅም ላይ ለሚያውሉ ኩባንያ ትልቅ ጥቅም የሚሰጥ እና የስራ እድሎችን የሚፈጥር ነው” ሲል በኢትዮጵያ የኮካ ኮላ መጠጦች አፍሪካ  ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዳሪሊ ዊልሰን በትላንትናው እለት በተካሄደው የመክፈቻ ዝግጅት ላይ ተናግሯል።

የኮካ ኮላን ተነሳሽነት ያደነቁት የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ እሸቱ ለማ በበኩላቸው  “ፕላስቲኮችን መሰብሰብ ከተማዋን ከማፅዳት ባለፈ ለሚሰበስበው አካል ዘላቂ ገቢ ያስገኝለታል” ብለዋል።

ኩባንያው በመላ አገሪቱ የፕላስቲክ ማሰባሰቢያ ማዕከላትን በማቋቋም ከ15,000 በላይ ሴት ሰብሳቢዎችን አሰልጥኖ ማብቃቱን ገልጧል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.