የዜና ትንተና፡የአፍሪካ ህብረት እና የትግራይ ክልል አፋጣኝ ያለ ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ያስፈልጋል ሲሉ፤ መንግስት “የመከላከያ እርምጃዉን” እቀጥላለሁ አለ

በትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ የኩናማ ማህበረሰብ አባላት ከባድ ጥቃት ደርሶባቸው ከቀያቸው ተፈናቅለው በቅርቡ በDW ቴሌቪዥን ቀርበዋል።

አዲስ አበባ ጥቅምት 07, 2015: የፌደራል መንግስት “የህወሓትን ተደጋጋሚ ጥቃት እና ከውጭ ሃይሎች ጠላት ጋር እያደረገ ያለውን ትብብር” በመቃወም የመከላከል እርምጃውን እንደሚቀጥል ገለጸ።

የኢትዮጵያና የኤርትራ ጦር ኃይሎች በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ እና አካባቢው ሰሞኑን ባደረሱት ጥቃት በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰዉን ጉዳት ተከትሎ እየጠነከረ በመጣው ዓለም አቀፍ ስጋት እና ውግዘት መሀል የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማሃማት  በትግራይ ክልል አፋጣኝ፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም እና የሰብአዊ አገልግሎት እንደገና መጀመር አንዳለበት” ጠይቀዋል።

ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የቀረበ ተመሳሳይ ጥሪዎችን ያስተጋቡት ሊቀመንበሩ እሁድ እለት በሰጡት መግለጫ ድርጅታቸው በትግራይ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በከፍተኛ ሁኔታ እየተከታተለ መሆኑን ገልጸው ተፋላሚ ወገኖች በአፍሪካ ህብረት የሚመራ ሰላማዊ ውይይት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ነገር ግን የአፍሪካ ህብረት መግለጫ እንደ አብዛኛው የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የኤርትራ ሃይሎች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ጥሪ አላቀረበም።

የአፍሪካ ህብረት ያቀረበው አስቸኳይ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ጥሪ በትግራይ ሀይሎች ተቀባይነት በማግኘቱ ጥሪውን እንደሚቀበሉ እና “በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት ተገዢ ለመሆን ዝግጁ ነን” ብለዋል። 
“የኤርትራ ጦር ከትግራይ እንዲወጣ፣ ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ተግባራዊ እርምጃ እንዲወስድ እና የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ድርድር እንዲመጣ ግፊት እንዲያደርግ [አለም አቀፍ ማህበረሰቡ] ጥሪ እናቀርባለን አንዲሁም የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም እንዲያደርግ ወይ የትግራይ ህዝብ ራሱን እንዲከላከል ድጋፍ ያድርግለት በማለትም ጠይቋል።

ቅዳሜ እለት የአለምአቀፉ ሬስኪዉ ኮሚቴ (አይአርሲ) ከእርዳታ ሰራተኞቹ መካከል አንዱ አርብ በሽሬ በተፈጸመ ጥቃት መሞቱን አረጋግጧል። በጥቃቱ ሌላ የአይአርሲ ሰራተኛም ቆስሏል፤ በድርጊቱም ሌሎች ሁለት ሰላማዊ ሰዎች መሞታቸው እና ሶስት መቁሰላቸው መግለጫው አክሎ ገልጿል።

ይህ በትግራይ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ በስራ ላይ የተገደሉትን የሰብዓዊ እርዳታ ሰራተኞችን ቁጥር 24 አድርሶታል።ባለፈው አመት መስከረም ላይ ተጨማሪ 11 የሪሊፍ ሶሳይቲ ኦፍ ትግራይ (REST) የተሰኘ በትግራይ ውስጥ ያለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የእርዳታ ሰራተኞች መገደላቸው ተከትሎ ቁጥሩ ከ12 ወደ 23 ከፍ ማለቱ ይታወሳል።

በሽሬ እና አካባቢው ከፍተኛ ተኩስ እና የአየር ድብደባ እንዲሁም የአይአርሲ ሰራተኞች መገደል ዘገባዎችን ተከትሎ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጦርነቱ እንዲቆም እና የኤርትራ ጦር ከትግራይ እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።

ቅዳሜ ጥቅምት 5 ቀን፣ አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል በሽሬ ዙሪያ በተከሰተው ግጭት፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያለ አግባብ እየተወሰደ ያለውን ጥቃት፣ የሰው ህይወት መጥፋት እና ውድመት አንዳሳሰባት አስታውቃለች። 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በትግራይ ያለው ጦርነት መባባስ በጣም እንዳሳሰባቸው እና ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቀዋል።

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ጆሴፕ ቦሬል “በትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ኢላማ ያደረገንዉና እየቀጠለ የመጣው ጥቃት አስግቶኛል ብለዋል። 

የአሜሪካው የአርዳታ ድርጅት (የዩኤስኤአይዲ) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በበኩላቸው “በሰሜን ኢትዮጵያ ሽሬ ከተማ በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው መጠነ ሰፊ ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት እንዲሁም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት በቅርቡ ባደረሱት ጥቃቶች ስጋት እንዳደረባቸው ተናግርዋል። የትግራይ መከላከያ ኃይል በአማራ ክልል እየወሰደ ያለው ቀስቃሽ እርምጃ በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ከፍተኛ ስጋት እያባባሰው ነው ሲሉ አክሎ ገልጸዋል።


መንግስት “የመከላከያ እርምጃዎችን መውሰዱን ይቀጥላል”

የፌደራል መንግስት በሰጠው ምላሽ “የህወሓት ተደጋጋሚ ጥቃት እና ከጠላት የውጭ ሃይሎች ጋር እያደረገ ያለውን ትብብር” በመቃወም የመከላከል እርምጃውን እንደሚቀጥል ዛሬ ማለዳ ላይ መግለጫ ሰጥቷል።
መንግስት በክልሉ የሚገኙ አየር ማረፊያዎችን እና ሌሎች የፌዴራል ተቋማትን በአስቸኳይ መቆጣጠር የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሶ ሰላማዊ ዜጎች እና የተራድኦ ድርጅት ሰራተኞች የትግራይ ኃይሎች ወታደራዊ ንብረት ከሉበት ቦታ አንዲርቁ ጥሪ አቅርቦዋል።

ሰላማዊ ዜጎች እና የተራድኦ ድርጅት ሰራተኞች ላይ ደረሰ የተባለውን ጥቃት አስመልክቶ አስተያየት ሲሰጥ, መንግስት ድርጊቱን እንደሚያጣራ ገልጿል:: 
“የኢትዮጵያ መንግስት በሰላማዊ ሰዎች እና የእርዳታ ድርጅት ሰራተኞች ላይ ስለደረሰዉ ጉዳት ከልቡ ያዝናል። እንዲህ ያሉ ጉዳዮችን በማጣራት እንደዚህ አይነት ያልተፈለገ ጉዳት ሲደርስ ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል” ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል። 

የኢትዮጵያ መከላክያ ሰራዊት በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግን በጥብቅ ያከብራል አንዲሁም  በከተሞች አካባቢዎች ውጊያዎችን አያደርግም ይላል መግለጫዉ::
ነገር ግን በተመሳሳይ መግለጫ መንግሥት በአፍሪካ ኅብረት በሚመራ የሰላም ድርድር ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል።

በአፍሪካ ህብረት መሪነት ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ/ም አሁድ በደቡብ አፍሪካ ሊደረግ ታስቦ የነበረዉ የሰላም ድርድር በሎጂስቲክስ ጉዳዮች ምክንያት መዘግየቱ ይታወሳል::

የአፍሪካ ህብረት ግን የዘገየበትን ምክንያት በተመለከተ የሰጠው መግለጫ የለም። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.