ዜና ፡- የህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች በንብረት ላይ የሚጣለውን ግብር ማን መወሰን አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1/2015 ዓ.ም፡- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች በጋራ በተገኙበት በንብረት ላይ የሚጣለውን ግብር ማን መወሰን አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ በትላንትናው እለት ምክክር አድርገዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፌስቡክ ገጹ እንዳለዉ ምክክሩ ያስፈለገዉ በሕገ መንግሥቱ ውስጥ በንብረት ላይ ታክስ የመጣል ስልጣን ለፌዴራልም ሆነ ለክልል መንግሥታት በግልጽ ተለይቶ ያልተሰጠ በመሆኑ ነዉ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 99 ላይ ለፌዴራልም ሆነ ለክልል መንግሥታት በግልጽ ተለይቶ ያልተሰጠው ግብርና ታክስ የመጣል ስልጣን ውሳኔ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጋራ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ድጋፍ ማግኘት እንዳለበት በግልጽ መቀመጡን ተናግረዋል።

የምክክሩ ዓላማም ምክር ቤቶቹ ውሳኔ ከማሳለፋቸው በፊት በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ግንዛቤ ለማግኘት ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡ ለምክክር መድረኩ ዶ/ር ሲሳይ ረጋሳ በንብረት ላይ የሚጣለውን ግብር ማን መወሰን አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ መነሻ ጽሑፍ አቅርበው ውይይት የተደረገበት መሆኑም ተጠቅሷል።

ሀገሪቱን ከድህነት ለማላቀቅና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ክልሎችና የፌዴራሉ መንግሥት አዳዲስ የገቢ ምንጮችን በጥናት ላይ ተመስርተዉ በማረጋገጥ፣ የሕግ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች ለይቶ በማሻሻል ወይም አዳዲስ ሕጎችን በማካተት ገቢ የመሠብሰብ አቅማቸውን አሟጥጠው መጠቀም እንደሚኖርባቸው በመድረኩ ላይ ተጠቁሟል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.