አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16/2015 ዓ.ም፡- ጥቅምት 15 የወጣው የአለም አቀፍ የፍትህ ፕሮጀክት (WJP) የህግየበላይነት ምዘና እንደሚያሳየው የኢትዮጵያ የህግ የበላይነት ምዘና ውጤት በዚህ አመት አጠቃላይ ኢንዴክስበ3.6 በመቶ ዝቅ ብሏል፡፡ ኢትዮጵያ ካለፈው አመት በአንድ ደረጃ ዝቅ በማለት ከአለማችን 140 ሀገራት 123ኛደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
እንደ የአለም አቀፍ የፍትህ ፕሮጀክት ሪፖርት፤ ኢትዮጵያ የሥርዓት እና የደህንነት ምዘና መቀነስን ጨምሮ ጉልህአዝማሚያዎች እያጋጠማት ነው።
ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ካሉ 34 ሀገራት 27ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በቀጣናው ከፍተኛ አፈጻጸምያስመዘገበችው ሩዋንዳ ስትሆን (በአለም አቀፍ ደረጃ ከ140 ሀገራት 42ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች)፤ ሞሪሺየስ እናናሚቢያ ከሩዋንዳ በመቀጠል ጥሩ አፈፃፀም አሳይተዋል።
በቀጣናው ዝቅተኛ ነጥብ ያስመዘገቡት ሀገራት ሞሪታኒያ፣ ካሜሩን እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሲሆኑበአለም አቀፍ ደረጃ 137ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
ከባለፈው አመት ከሰሃራ በታች ካሉት 34 የአፍሪካ ሀገራት 20 የሚሆኑ ሃገራት ደረጃቸው ዝቅ ብሏል። ከእነዚህ20 አገሮች ውስጥ 15ቱ የቀነሰው ባለፈው ዓመት ነው።
ኢትዮጵያ፤ አፍጋኒስታን፣ ቡርኪናፋሶ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ጋምቢያ፣ ጊኒ፣ ላይቤሪያ፣ ማዳጋስካር፣ ማላዊ፣ማሊ፣ ሞዛምቢክ፣ ኒጄር፣ ሩዋንዳ፣ ሴራሊዮን፣ ሱዳን፣ ቶጎ እና ኡጋንዳን ጨምሮ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው 17 ሀገራትውስጥ 13ኛ ሆናለች።
በአለም ዙሪያ 140 ሀገራትን እና የአለምን የህግ ስልጣንን የገመገመው የአለምአቀፍ ፍትህ ፕሮጄክት መረጃእንደሚያሳየው በዚህ አመት ኢትዮጵያን ጨምሮ በተገመገሙ ሀገራት 61 በመቶ የህግ የበላይነትን ማክበርቀንሷል።
“የግምገማ ውጤት እንደሚያሳየው ከኮቪድ ወረርሽኝ በፊት የነበሩት አምባገነናዊ ሂደቶች፤ ለምሳሌ በህግአስፈፃሚው አካል ላይ ያሉ ደካማ ፍተሻዎች እና በመገናኛ ብዙሃን ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች ፣ በአለም ዙሪያ የህግየበላይነትን እየሸረሸሩ ቀጥለዋል” ሲል የገለፀው የአለም አቀፍ የፍትህ ፕሮጀክት የሕግ የበላይነትን የሚገልፀውዘላቂ የሕግ፣ የተቋማት፣ የመተዳደሪያ ደንብ እና የማኅበረሰብ ቁርጠኝነት ተጠያቂነት፣ ፍትሐዊ ሕግ፣ ግልጽመንግሥት እና ተደራሽ ፍትሕ ነው ብሏል።
ነገር ግን፣ የአሁኑ የፍትህ ስርዓት ማሽቆልቆሉ ከአምናው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአስደናቂ ሁኔታ ከተረበሸው እናመንግስታት የዜጎችን ነፃነቶች ለመግታት እና ግልፅነትን ለማዳከም ከጣለበት ጋር ሲነፃፀር ያነሰ ነው፡፡
እንደ መረጃ ጠቋሚዎች በዚህ ዓመት ከተከሰቱት ታላላቅ አለም አቀፋዊ ውድቀቶች ውስጥ ጥቂቶቹ ከጊዜወደጊዜ እየጨመረ የመጣው አምባገነንነት እና የህግ የበላይነት መሸርሸር ጋር ተያይዞ የመጡ ምክኒያቶችናቸው፡፡ “በዚህ ዓመት የመሰረታዊ መብቶች መከበር በሃገራቶች በሁለት ሶስተኛ ቀንሷል፡፡
በመንግስት ስልጣን ላይ በተገረገ ፍተሻ በህግ አውጭዎች እና በመገናኛ ብዙሃን ላይ በዚህ ዓመት 58 ፕርሰንትበሚሆኑ ሃገራቶች ቀንሷል፤ በአለም አቀፍ ደረጃ 4.4 ቢሊዮን ሰዎች የህግ የበላይነት በተዳከመበት አካባቢዎችይኖራሉ” ብሏል የአለም አቀፍ የፍትህ ፕሮጀክት፡፡
የአለም አቀፍ የፍትህ ፕሮጀክት ዋና ዳይሬክተር ኤልዛቤጥ አንደርሰን “ካጋጠምን ወረርሽኝ አየወጣን ቢሆንምአለም አቀፉ የህግ የበላይነት ውድቀቱ ግን ቀጥሏል› ብለዋል፡፡ የህግ የበላይነት ከልብ የመነጨ ፍትሐዊነትማለትም ተጠያቆነት፣ እኩልነት እና ለሁሉም እኩል ፍተህ ነው፡፡ ፍትሃዊነት በሌለበት አለም ተለዋዋጭነትየማይቀር ነው” ብለዋል፡፡አስ