ዜና፡ የሶማሌ ክልል ምክር ቤት አባል ወ/ሪት ጁዌሪያ መሀመድ ከአንድ የፖሊስ አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አለፈ

ወ/ት ጁዌሪያ መሀመድ ኢብራሂም


አዲስ አበባ፣ጥቅምት16/ 2015 ዓ.ም፡-የሶማሌ ክልል ምክር ቤትና የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ት ጁዌሪያ መሀመድ ኢብራሂም በሶማሊ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ ውስጥ ከፌደራል ፖሊስ አባል በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉን የሶማሌ ክልል ኮምንኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

በተጓዦች እና በፖሊስ አባላት በተፈጠረው አለመግባባት በተከፈተው ተኩስ ወ/ሪት ጁዌሪያ ወድያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ አህታቸውን ጨምሮ ሌሎች አራት ሰዎች መቁሰላቸው መረጃ ከቦታው አግኝቻለው ሲሉ የጁዌሪያ ጓደኛ ዶ/ር ጁዌሪያ አሊ ተናግረዋል።

የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፌ አቶ መሓመድ ጉራይ ድርጊቱ በጅግጅጋ ጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አየር ማረፊያ በትላንትናው ዕለት ከቀኑ 10፡00 መፈጸሙን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀው ዝርዝር መረጃውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን አንደሚያሳውቅ ተናግረዉ ነበር።

የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በድህረ-ገፁ ባወጣው መግለጫ አንድ የጸጥታ አባል በተኮሰው ጥይት ወ/ት ጁዋሪያ ህይወታቸው ማለፉን ገልፆ በተኩሱ የቆሰሉ ሌሎች አራት ዜጎችም በህክምና ተቋማት እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል ብሏል። 

ድርጊቱን የፈፀመው ተጠርጣሪ በክልሉ የፀጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ስር ውሎ  ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ አክሎ ገልጧል።

የብልፅግና ፓርቲ በበኩሉ የፓርቲዉ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወ/ሮ ጁዋሪያ መሀመድ ኢብራሂም በጅግጅጋ ኤርፖርት  ውስጥ ከአንድ የፀጥታ ሀይል አባል በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ገልፆ ጉዳዩ በህግ አግባብ ተይዞ  እየተጣራ ነዉ ብሏል::

ከድረጊቱ በኋላ በኤርፖርት የተፈጠረውን ክስተት ወዳያውኑ በቁጥጥር ስር በማዋሉ ኤርፖርቱ ወደ መደበኛ ስራው ተመልሷል ያለው የክልሉ ኮምንኬሽን ቢሮም፤  የክልሉ መንግስት ጉዳዩን በመመርመር ወደፊት ለህዝብ ይፋ ያደርጋል ሲል አስታውቋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.