ዜና ትንታኔ፡ ከኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ጋር በተፈጠር ግጭት በ19 የፖሊስ አባላት ላይ ጉዳት ደረሰ፤ በሻሸመኔ ከተማ በምዕመናንን እና ፖሊስ መካከል በተፈጠረው ግጭት “በርካታ ሰዎች” ሞተዋል፤ መንግስት “ህገወጥ” የተባሉትን ቡድን ከመደገፍ እንዲቆጠብ ሲኖዶሱ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30/ 2015 ዓ.ም፡- በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞን ድንበር በተለምዶ ፊሊዶሮ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቅድስት ለደታ ቤተ ክርስቲያን የተሰበሰቡ ሰዎች “የታሰሩ ሰዎች ይፈቱ” በማለት መንገድ በመዝጋት የፀጥታ ችግር ኢንዲከሰት በማድረግ በ19 ፖሊሶች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ማድረሳቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ፖሊስና የቤተ ክርስቲያኗ አባቶች የታሰረ ሰው አለመሆሩን በመግለፅ መንገዱን እንዲከፍቱ ጥረት ቢደረግም ፈቃደኛ አልሆኑም ሲል የገለፀው ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በወቅቱ ተዘግቶ የነበረው መንገድ እንዲከፈትና ሰላማዊ እንቅስቃሴው እንዲቀጥል ተደርጓል ሲል ፖሊስ ትላንት ምሽት ባወጣው መመግለጫ ገልጧል፡፡

በወቅቱ ግጭቱ እንዲፈጠር በግልፅም ሆነ በስውር ሲቀሰቅሱና በተባባሪነት ሲሳተፉ በነበሩ ሃይሎች በተወረወረ ድንጋይ በ19 የፖሊስ አመራርና አባላት ላይ ከከባድ እስከ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል ያለው ፖሊስ ወቅታዊ ሁኔታን እንደ ሽፋን በመጠቀም ግጭት እንዲቀሰቀስ የሚሰሩ አካላት የከተማችንን ሰላም ከሚያደፈርስ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሻሸመኔ ከተማ  ቅዳሜ ጥር 27 በኦርቶዶክስ ምዕመናን እና በከተማ ፖሊስ መካካል በተነሳ ግጭት የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን የአይን እማኝ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፀ፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰው በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በአዲሱ “የኦሮሚያና ብሔሮች ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ” የተሾሙ አባላት የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ላይ በነበረበት ወቅት ነው።

አይን እማኙ በኦሮሚያና ብሔሮች ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ የተሾሙት አቡነ ጳውሎስ በምእራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ለማገልገል ወደ ሻሸመኔ ከተማ በማምራታቸው ግጭቱ መቀስቀሱን ገልፀው የቤተክርስቲያኒቱ አማኞች የተሶሙትን ጳጳስ እና ቡድናቸውን በመቃም አቀባበል እንዳልተደረገላቸው  ተናግረዋል፡፡

ጠዋት 2 ሰዓት ሲሆን በከተማዋ ውስጥ ያሉ ሁሉም ቤተ ክርስቲያን ደወል በመደወል ምእመኑ የተሰበሰበ ሲሆን ይህን ተከትሎ በክልሉ ልዩ ሃይሎችና በምእመኑ መካከል በተነሳ ግጭት ሁለት ሰዎች ወዲያው በፖሊስ በተቶከሰ ጥይት መገደላችውን በስፍረው ነበርኩ ያለው ዓይን እምኙ ገልጧል፡፡

 “ደውሉን እንተሰማ ምእመናኑ ወደ ቅዱስ ሚካዔል ቤተ ክርስቲያን መሄድ ጀመሩ፡፡ የከተማው ፖሊስ ህዝቡን ለመበተን መሳርያ በመቶከስ ሲጀም ነበር ሁለት ወጣት ልጆች የተገደሉት፡፡ ሎሎች አራት ሰዎች መቁሰላቸውንም አይቻለው” ሲል አስረድቷል፡፡

የሟቾቹን ትክክለኛ ቁጥር ማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም የቤተክርስቲያኗ ሚዲያዎች የማቾቹ ብዛት ከ35 በላይ እንደሚደርስ ዘግበዋል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሃፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ከአንከር ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ቁጥሩ እስከ 30 መድረሱን ተናግረዋል።

ከቅዳሜው ውጥረት በኋላ በሁኑ ሰዓት ከተማዋ በአንጻራዊ መረጋጋት ውስጥ ትገኛለች።

ክስተቱን ተከትሎ ቅዱስ ሲኖዶሱ ባወጣው መግለጫ በሊቃነ ጳጳሳት፣ የሀገረ ስብከት ሥራ አኪያጆችንና ሠራተኞችን፤ አገልጋይ ካህናትንና ምእመናን ላይ እየደረሰ ያለውን ሕገወጥ እስራትና እንግልት በጽኑ አውግዟል። ቅዱስ ሲኖዶሱ በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ የሚገኘውን በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ በወጡት ምዕመናን ላይ ጥቃት መፈፀሙን ገልፆ የተፈጸመው ሕገ ወጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የተፈጸመው አሰቃቂ የሞት ድርጊትን አውግዟል፡፡

እንዲሁም በየካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ሥርዓተ ቅዳሴ ከተፈጸመ በኃላ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ አስታውቋል፡፡

የፌዴራል መንግስት ኮሙኑኬሽን አገልግሎት ጥር 28 ቀን ባወጣው መግለጫው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረው መለያየት ሰላማዊ በሆነ መንገድ፣ በውስጣዊ አሠራር መፈታት እንዳለበት መንግሥት ያምናል ሲል ገልጧል። ሁኔታውን ህዝባዊ አመፅ ለመቀስቀስ በሚጠቀሙ አካላት ላይ የህግ የማስከበር እርምጃ እንደሚወሰድም አስጠንቅቋል።

ይህ በእንዲህ እያለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የፌዴራል መንግስት ኮሙኑኬሽን አገልግሎት ያወጣውን መግለጫ እንደማትቀበለው አስታውቃለች፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ ባወጣችው መግለጫዋ፣ መንግስት “በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ” በሚል ርእስ የሰጠው መግለጫ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ክብር፤ ታሪክ ቸል ያለ ነው ብላለች፡፡ መግለጫው እውነታን ቸል በማለት በጉዳዩ ላይ የተሟላ መረጃ የሌላቸው ወገኖች የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲይዙ የሚያስችል መግለጫ ነው በማለት የማትቀበለው መሆኑን ገልፃለች፡፡

በመግስት የተሰጠው መግለጫ በሻሸመኔ ከተማ የተፈፀመውን ግድያ ያማያወግዝ እና ሀዘኑን የማይገልጽ መሆኑ የመንግስትን አቋም ያሳያል ስትል የገለፀችው ቤተ ክርስቲያኗ፣ መንግስት “ህገወጥ” የተባሉትን ቡድን ከመደገፍ እንዲቆጠብ እና እስካሁንም ለደረገው ድጋፍ ይቅርታ እንዲጠይቅ ጥሪ አቅርባለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ህዝበ ህርስቲያኑ፣ መንግስት ድጋፍ የሚሰጠውንና መፈንቅለ ሲኖዶስ ለማድረግ የሞከረውን ህገ- ወጡን ቡድን በመቃወም ከጥር 29 እስከ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓ.ም የሚቆውን ጾመ ነነዌን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ እንዲያሳልፍ ማዘዟ ይታወቃል፡፡

ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ ጥሪ ተላልፏል፡፡ጥቁር ልብስ የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው ሲል መግለጫው ገልጧል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ መንግሥት ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር አልቻለም ሲል ወቅሶ፣ ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን በመማፀን ጸሎትና ምሕላ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተረድቷል ብሏል።

ባሳለፍነው ሳምንት ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለሚኒስትሮችና ለካቢኔዎቻቸው ማብራሪያ ዝምታቸውን በመስበር የቤተክርስቲያኗ መሪዎች ልዩነታቸውን በንግግርና በምክክር እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ማንም የካቢኔ አባል እዚህ ውስጥ እጁን እንዳያስገባ በማለት ቢያሳስቡም  ኢዜማ ባወጣው መግለጫ ገዢው ፓርቲ አዲስ የተሸሙትን ሊቃነ ጳጳሳትን በማገዝ ቤተ ክርስቲያኗን ለመከፋፈል እየሰራ ነው በማለት ተችቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያውን የሰጡት መንግስታቸው አዲስ የተሸሙትን ሊቀ ጳጳሳት እየደገፈ ነው የሚሉ እና አዲሶቹን ሊቃነ ጳጳሳት የተቃሙ የሃይማኖት መሪዎች ላይ የፀጥታ አካላት እስር እና ጫና እያደረጉ ነው የሚሉ ትችቶች እየጨመሩ በመጡበት ወቅት ነው።

በቤተክርስቲያኗ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ በጥር 23 ቀን 2015 ዓ.ም ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለሚኒስትሮችና ለካቢኔዎቻቸው የሰጡት የወቅታዊ ጉዳይ ማብራሪያን በመቃወም ቅዱስ ሲኖዶስ  ጥር 24 የምላሽ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫውም ቤተክርስቲያኗ አቋሟን በዝርዝር ያስቀመጠች ሲሆን ጠ/ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው የጠቀሷቸው ማብራሪያዎች አሳሳቾች ናቸው ስትል ተችታለች። እርምት እንዲወሰድባቸውም አሳስባለች። ቅዱስ ሲኖዶስ መንግሥት በሕገ መንግሥቱ የተጣለበትን ኃላፊነት በመወጣት የቤተ ክርስቲያኒቱን ተቋማዊ ልዕልና እንዲያስጠብቅ እንዲሁም ህገ ወጡን ድርጊት ተገቢውን እርምት እንዲሰጥ አሳስቦ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ አገልጋይ ካህናትና ምእመናን ጭምር የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚካሄድ አስታወቀ፡፡

የቅዱስ ሲኖዶሱ እና የምእመኑ ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን አዲስ የተሸሙት ሊቀ ጳጳስ 25ቱን ተሸዋሚዎችን ወደ ተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አገረ ስብከት መላክ ቀጥለዋል። በተለያዩ አህጉረ ስብከት የተመደቡ ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት እየተላኩ እና በየአካባቢያቸውም ሆነ በመንገዶቻቸው ምእመናን አቀባበል እየተደረገላቸው መሆኑን የኦሮሚያና ብሔሮች ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ ቃል አቀባይ ኃይለሚካኤል ታደሰ ገልጸዋል።

ዳራ

ጥር 18/ 2015 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከቀኖና እና ከእውቅናዬ ውጭ የሆነ ሕገ ወጥ የኤጲስ ቆጶሳት እና ጳጳሳት ሹመት ተስጥቷል በተባለው ጉዳይ ላይ ቅዱስ ሲኖዶሱ ባካሄደው አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ፣ ሲመቱን በሰጡ ሶስት ሊቀጳጳሳት እና 25 ተሿሚዎች ላይ የውግዘት ውሳኔ አሳለፈ።  የተወገዙት ሶስቱ  ጳጳሳት እና 25 ኤጴስ ቆጶሳት እሁድ ጥር 20 በምላሹ 12 የነባሩን ሶኖዶስ አባላትን በማውገዝ የራሳቸውን ኤጴስ ቆጶሳት በመሾም ወደ ተመደቡበት ሀገረ ስብከት እየተሰማሩ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ቤተክርስቲያኗ ለሁለት እንድትከፈል እያደረገ ያለው ክስተት፣  በኦሮምያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በሶዶ ዳጬ ወረዳ በወሊሶ ከተማ በበአለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን በአቡነ ሰውሮስ እና ሌሎች ሁለት ጳጳሳት መሪነት በርካት ህዝበ ክርስቲያንን ያስቆጣው  ለኦሮሚያ ክልል 17 ጳጳሳት እንዲሁም 9 ጳጳሳት ከኦሮሚያ ውጭ በጥቅሉ 26 ጳጳሳትን ከቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቀኖና ውጭ መሾማቸው ነው፡፡

አቡነ ሳዊሮስ በዓለ ሲመቱ ከተከናወነ በኋላ በሰጡት መግለጫ ሲመቱን ለመፈጸም ያበቋቸውን አስገዳጅ ሁኔታዎች መዘርዘራቸው ይታወሳል። ከተዘረዘሩት ምክንያቶችም መካከል በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች የቤተክርስቲያኗ ተከታዮች አገልግሎት ለማግኘት ያስችላቸው ዘንድ አከባቢያቸውን የሚያውቁ እንዲሁም ቋቋቸውን የሚናገሩ አገልጋዮች ሊኖራት እንደሚገባ አመላክተው ይህ ባለመደረጉ ቤተክርትሲያኗ በተለይም በኦሮምያ እና ደቡብ ክልል በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማኞቿን አጥታለች የሚለው ይገኝበታል።

የጳጳሳቱ ሹመቱ ከሲኖዶሱ እውቅና ውጭ የተደረገ ህገ-ወጥ ሹመት ነው ያሉት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ድርጊቱ “በቤተ ክርስቲያን ላይ ያነጣጠረ ታላቅ ክስተት” ነው በማለት አስቸኳይ ምልአተ ጉባኤ መጥራታቸው ይታወሳል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.