አዲስ አበባ፣ የካቲት 22/ 2015 ዓ.ም፡- በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለሁለት ዓመታት በዘለቀው ደም አፋሳሽ ጦርነት ምክንያት ከአንድ የትግራይ አካባቢ ተፈናቅለው ወደ በሌላ የትግራይ አካባቢ የተጠለሉ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ከዕለት ተዕለት እየጨመረ በመምጣቱ የተነሳ ለእለት ጉርሻ ዕርዳታ የሚሹ ተፈናቃዮች ቁጥር እያሻቀበ የመጣ ሲሆን ተፈናቃዮቹ መንግስት እና የእርዳታ ድርጅቶች ለእለት ጉርስ የሚሆን እርዳታ እያደረሱልን አይደለም የሚል ቅሬታ ያቀርባሉ፡፡
ባልተገደበ ሁኔታ የሰብዓዊ ዕርዳታ ወደ ክልሉ እየደረሰ መሆኑን በፌዴራል መንግሥት፣ በትግራይ ባለሥልጣናት እና በሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች በተለያየ ወቅት የተገለጸ ቢሆንም፣ በመቀሌ የሚገኙ ተፈናቃዮችና አስተባባሪዎቻቸው ግን የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ በወቅቱ እየደረሰላቸው ባለመሆኑ ለችግር እየተዳረጉ በመሆኑን መፍትሄ እንዲደረግላቸው ይጠይቃሉ።
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት (UN OCHA) እንዳስታወቀው በሰሜን ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ከ127,000 ሜትሪክ ቶን በላይ የምግብ አቅርቦት ወደ ትግራይ መድረሱን በመጥቀስ ከህዳር አጋማሽ እስከ ጥር አጋማሽ ባለው ወቅት መድረሱንና የሰብአዊ አቅርቦት መሻሻል እንዳሳየ አስታውቋል።በመግለጫው መሰረት “ከ4.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ወይም 83 በመቶ ለክልሉ ከታቀደው 5.4 ሚልዮን የጉዳት መጠን ውስጥ 83 በመቶው በሁለተኛው ዙር የምግብ እርዳታ ስርጭት መደረጉን ያመለከተው ሪፖርቱ ከእነዚህም መካከል ከ162,000 በላይ የሚሆኑት ተፈናቃዮች እንደሆኑ አመልክቷል።
በመቀሌ የሚገኙ ተፈናቃዮች ግን ባለፉት ሶስት ተከታታይ ወራት ምንም አይነት የምግብ እርዳታ አለማግኘታቸውን እና በክልሉ እየታየ ያለውን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦታ መሻሻል መሻሻል ጋር ተያይዞ እየቀረበ ያለ ዘገባ ትክክል አለመሆኑን ይናገራሉ፡፡
አቶ ሰለሞን ኪሮስ የ47 ዓመት ጎልማሳ ናቸው፡፡ ከስምንት ቤተሰቦቻቸው ጋር ከምስራቅ ዞን አዲጎሹ ተፈናቅሎ አሁን በመቀሌ ሰባ ቃሬ በሚባል ግዚያዊ የተፈናቃዮች ማረፊያ ላይ ይገኛሉ።
እንደ አቶ ሰለሞን ከሆነ በስፍራው ያሉ ተፈናቃዮች ከሶስት ወራት በፊት ከተሰጣቸው 15 ኪሎ ስንዴ ውጭ ምንም ዓይነት ሰብዓዊ እርዳታ ባለማግኘታቸው በምግብና በመድኃኒት እጦት ለከፋ ችግር እየተዳረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
“ተፈናቃዮች መጠለያም ሆነ አስፈላጊ የማብሰያ ዕቃዎች ስለሌላቸው እና እርዳታ ስለማያገኙ በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ ናቸው” ይላሉ። አቶ ሰለሞን አያይዘውም አብዛኞቹ ተፈናቃዮች ሰብአዊ እርዳታ ላይ “ጥገኛ መሆንን አይፈልጉም ይልቁንም ወደ ቀያቸው ተመልሰው በኢኮኖሚ ራሳቸውን መርዳት እና የራሳቸዉን ፍጆታ መሸፈን ነው የሚፈልጉት” ብለዋል።
በትግራይ ክልል ባለስልጣናት እና በፌዴራል መንግስት መካከል በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት ያሉበት መከራ ያበቃ ዘንድ መንግስት ወደ ቀያቸው እንዲመልሳቸው ይማጠናሉ።
አቶ ሳሙኤል ተከለ ሃይማኖትም ዓዲ ሓውሲ በሚባል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግዚያዊ የተፈናቃዮች ማቆያ ከተጠለሉ ሰዎች አንዱ ናቸው። የነበረውን አስከፊ ጦርነት ሸሽተው ነበር ከቃፍታ ሁመራ ወደ መቀሌ ከሰባት ቤተሰቦቻቸው ጋር በ 2013 ዓም እሳቸውም በተመሳሳይ መልኩ ምንም ዓይነት ሰብዓዊ እርዳታ አያገኙም አለመሆኑን ይናገራሉ።
ሳሙኤል ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገረው “ምንም ነገር አላገኘንም። 15 ኪሎግራም ስንዴ ከተሰጠን በህዋላ አሁን ሶስተና ወራችን ነው” ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ የተናገሩት ተፈናቃዩ “ቅሬታችንን ለዞኑ እና ለትግራይ ክልል ባለስልጣናት ብናሳውቅም ሁሌም በቅርቡ እንደሚሰጡን ይናገሩ እንጂ እስከ አሁን ምንም አዲስ ነገር የለም” ብለዋል።
ተፈናቃዮቹ የምግብ፣ የመድኃኒት እና ምግብ ነክ ያልሆኑ የፍጆታ አቅርቦት እጥረት ገጥሞናል በማለት ያቀረቡትን ቅሬታ በተመለከተ የመቀሌ ተፈናቃዮች ድጋፍ ረዳት ዳይሬክተር ዶክተር ሰለሞን ጸጋይ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት፤ “ተፈናቃዮቹ እያቀረቡ ያለው እርዳታ መሬት ላይ ያለ በእውነቱ” መሆኑን አረጋግጠዋል።
ረዳት ዳይሬክተሩ እንዳረጋገጡት ተፈናቃዮቹ ከመጀመሪያው ዙር በስተቀር ባለፉት ሶስት ወራት ምንም አይነት እርዳታ አላገኙም። ይህ ሊሆን የቻለበትን ምክንያት ሲያብራሩ ደግሞ “በዋነኛነት በተመደበው ኮታ እና በተጨባጭ ያሉን ተፈናቃዮች ቁጥር መካከል አለመጣጣም በመፈጠሩ ምክንያት የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መዘግየቴን አስረድተዋል”
ከመጀመሪያው ዙር በወሰድነው ትምህርት መሰረት የተፈናቃዮቹን መረጃ በትክክል አዘጋጅተን ለአለም የምግብ ፕሮግራም አቅርበን የነበረ ቢሆንም የድርጅቱ ባለስልጣናትበራሳቸው በኩል የተጠናቀረውን ቁጥር ስራ ላይ በማዋላቸው የእርዳታ አሰጣጡ ላይ መንጠባጠብ መፈጠሩን አስረድተዋል።
“ባደረጉት ቃለ ምልልስ እና በመረጃ አሰባሰብ ወቅት ባጋጠመ ችግር ምክንያት እነሱ ያሰባሰቡት እና እኛ በሰጠናቸው መረጃ መካከል አለመጣጣም በማጋጠሙ ምክንያት ነው የእርዳታ ክፍፍል መዘግየት የተፈጠረው” ሲል ዶክተር ሰለሞን ተናግሯል።
ረዳት ዳይሬክተሩ አያይዘውም የረድኤት ድርጅቶቹ የተሰጣቸውን የተፈናቃዮች ቁጥር በመውሰድ ቀደም ሲል በአግባቡ ያልተሰበሰበውን መረጃ በማጤን በክልሉ ያሉት የተፈናቃዮች ትክክለኛ ቁጥር ሊጠቀሙ እንደሚገባ ተናግረዋል።
ዶክተሩ አያይዘውም “በመቀሌ ብቻ 1 መቶ 84 ሰማኒያ ሺህ ተፈናቃዮች ያሉ ሲሆን የእርዳታ ድርጅቶች ግን ያቀረቡልን እርዳታ ለ139,850 ሰዎች ብቻ በመሆኑ 44,150 ሰዎች ከተሰጠን ኮታ ውጪ ሆኖውብናል” ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግሯል።
በመቀሌ የሚገኙ ተፈናቃዮች በጊዜያዊ አስተዳደር ጊዜ የመጡ ሆነው በእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች የተመዘገቡ፣ የትግራይ ታጣቂዎች መቐለን ዳግም በያዙበት ወቅት ከሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው የመጡ እና የኤርትራ ወታደሮች ባደረሱባቸው አረመኔያዊ ግፍ ከሰላም ስምምነቱ በህዋላ የተሰደዱ መሆናቸውን ረዳት ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ተፈናቃዮቹ ከየክልሉ ማእዘን እንደ ሰሜን ምስራቅ ዞን፣ምስራቅ ዞን፣ምዕራብ እና ማዕከላዊ ዞን በተለይም ከደቡብ ምዕራብ ዞን አከባቢዎች ወደ መቀሌ የመጡ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
ከመቀሌ የተፈናቃዮች ማእከል የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ወቅት በመቀሌ ብቻ በድምሩ 3 መቶ ሺህ ተፈናቃዮች ሲኖሩ ከነዚህ መካከል ከ20 በላይ በሚሆኑ ግዚያዊ መጠለያዎች የሚሆኑ ተፈናቃዮች የምግብ እና የምግብ ነክ ያልሆኑ ነገሮች ድጋፍ አላገኙም።
በተመሳሳይ መልኩ ከ54,000 በላይ ተፈናቃዮች በማዕከላዊ ትግራይ ዓብይ-ዓዲ በሚገኘው የተፈናቃኦች ካምፕ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን፤ የምግብ እና የመድሀኒት አቅርቦት እጥረት በመኖሩ ምክንያት ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወቃል።አስ