ዜና: በኦሮምያ ክልል ምሊሻዎችና በሶማሌ ክልል ነዋሪዎች መካከል በግድብ ግንባታ ምክንያት በተፈጠረው እለመግባባት የንጹሃን ዜጎች ህይወት ማላፉ ተገለጸ 

ኮማንደር አሊ ሳሚሬ ሲጋድ፤  ፎቶ- ከቪዲዮ የተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2015 ዓ.ም፦ ከኦሮሚያ ክልል የመጡ ሚሊሻዎችና በሶማሌ ክልል ነዋሪዎች መካከል በአዋሳኝ ድምበር ላይ በተፈጠረ አለመግባባት በትንሹ ሶስት ሰለማዊ ሰዎች ሲሞቱ 12 የሚሆኑ ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ነዋሪዎች ገለጹ። 

የሶማልያ ክልል ነዋሪዎች እንደገለጹት ከሆነ ግጭቱ የተቀሰቀሰው ጥር 7 ቀን 2015 ዓ/ም  በኦሮሚያ ክልል መንግስት የተላኩ ኣባላት በሶማሊ ክልል ማራር ቀበሌ፤ በቱሉ ጉሌድ ወረዳ የፋፋን ዞን ላይ የግድቡን ግንባታ ለመጀመር እንቅስቃሴ ማድረጋቸው ተከትሎ ነው።  

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅጋ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ቀበሌ የግድቡን ስራ በተናጠል በሶማሊ ክልል ውስጥ ለማስቀጠል ባደረገው እንቅስቃሴ ከአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ ገጥሞታል።

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ከፍተኛ ባለስልጣን ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት ግድቡ በሁለትም የማህበረሰብ እካላት በነበረው አለመግባባት በኦሮሚያና በሶማሊ ክልል ባለስልጣናት በተደረገው ውይይት  ከስምምነት ላይ ተደርሶ የግድቡ ግንባታ  ለግዜው እንዲቆም ተደርጎ ነበር። ነገር ግን ግልጽ ባልሆነ ምክንያት የግድቡ ግንባታ ሊጀምር ችሏል። 

በማራር ቀበሌ የሀገር ሽማግሌ የሆኑት ሙህያደን ሀጂ አቢብ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት “የግድቡን ፕሮጀክት ምክኒያት በማድረግ የኦሮሚያ ክልል ግዛቶቹን ወደ ሶማሌ ክልል እያስፋፋ ነው” ብለዋል።

አክለውም በጥር 7 ቀን 2015 ዓ/ም በኦሮሚያ ሚሊሻዎች ባደረሱት ጥቃት ሶስት ሰላማዊ ሰዎች ሲገደሉ 12 ሰዎች ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል። ከሶማሌ ክልል የተውጣጡ ሌሎች ሪፖርቶች የተጎጆዎች ቁጥር 16 እንደሚደርስ ይገልፃሉ። 

በአካባቢው የግድብ ግንባታ ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል መንግስት ይፋ የተደረገው ከስድስት ወራት በፊት መሆኑን የገለጹት አቶ ሙህየዲን፣ “ይህ እርምጃ በክልሎቹ መካከል እለመግባባት ሊያስከትል ይችላል በማለት ለሶማሊ ክልል መንግስትና ለሚመለከታቸው የባለድርሻ እካላት ስጋታችንን ስንገልፅ ቆይተናል” ብለዋል። 

የሶማሌ ክልል የድንበር ጉዳይና ግጭት አፈታት ቢሮ ኃላፊ ኮማንደር አሊ ሳሚሬ ሲጋስ ማክሰኞ እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ያለውን መልካም ወንድማዊ ግንኙነት ያለ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን የኦሮሚያ ክልል ፖለቲከኞች በድንበር አካባቢ ያሉ አካባቢዎችን ለማስፋት እየሰሩ ነው ሲሉ ከሰዋል።

አክለውም አሊ በሶማሌ ክልል ግዛት ውስጥ በሚገኘው ማራር ቀበሌ ከሶማሌ ክልል መንግስት ጋር ስምምነት ሳይደረግ እንዲሁም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ሳይመክሩ ግድብ ለመስራት እየሞከሩ ነው ብለዋል።

በግድቡ ግንባታ ምክንያት የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ከኦሮሚያ ክልል የተውጣጡ ታጣቂዎች ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውንና በርካቶች መቁሰላቸውን ጠቁመው፣ ግንባታው ቀደም ሲል ከ2000 በላይ የሚሆኑ የሶማሌ ማህበረሰብ አባወራዎችን ከአካባቢው ማፈናቀሉን ገልፀዋል።

ነገር ግን የሶማሊ ክልል መንግስት ኮሙኑኬሽን ቢሮ፣ ኮማንደር አሊ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ባለመቻላቸው ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ገልጾ ለሚዲያ የሰጡት መግለጫ ከሀላፊነት ከተነሱ በኋላ ተሰጥቷቸው የነበረውን ሀላፊነት በህጋዊ መንገድ ርክክብ ሳያደርጉ መሆኑን ገልጧል፡፡

ቢሮው አክሎ ግለሰቡ የሰጠው መግለጫ የክልሉን መንግሥት አቋም የማይወክልና ህገወጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡

አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንደገለፁት ከሳምንታት በፊት የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ግድቡ የሚገነባበትን ቦታ መጎብኘታቸውንና በማራር ቀበሌ ነዋሪዎች ላይ ውጥረት መፍጠሩን በመጨረሻም ከኦሮሚያ ክልል ከመጡ ታጣቂዎች ጋር ግጭት ማስከተሉን ገልፀዋል።

የኦሮሚያ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ምንም አይነት መረጃ የሌላቸው መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል።

ባለፈው አመት ታህሳስ ወር ላይ በሶማሌ ክልል ቆራሄ ዞን ሽላቦ ወረዳ የአካባቢው ባለስልጣናት የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ለመጀመር ሲሞክሩ በተፈጠረ አለመግባባት የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሰባት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱ ይታወሳልአስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.