ዜና፦ አሜሪካ 3 ሚሊየን ዶላር የሚገመቱ 126 የሳንባ ነቀርሳ መመርመሪያ ማሽኖችን ለኢትዮጵያ ለገሰች

አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን 126 የጄኔክስፐርት ማሽኖችን ለኢትዮጵያ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ሲያስረክቡ።

አዲስ አበባ፣ጥቅምት29/ 2015 ዓ.ም ፦ የአሜሪካ አለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (USAID) 157 ሚሊዮን ብር በላይ (3 ሚሊዮን ዶላር) የዋጋ ግምት ያላቸዉ 126 ‘ጄኔክስፐርት’ የተሰኘ የሰንባ ነቀርሳ መመርመርያ ማሽኖች ድጋፍ ለኢትዮጵያ አበረከተች።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ አንዳስታወቀው “ድጋፉ የኢትዮጵያ መንግስት የሰንባ ነቀርሳ (ቲቢ) እንዲሁም መድሃኒት የተላመደ ቲቢ (ኤምዲአር-ቲቢ) ኬዞችን በፍጥነትና በተሳካ ሁኔታ ለመለየትና ለመመርመር አያደረገው ላለው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል” ብሏል።

አዲሶቹ ማሽኖች ቲቢን ለመመርመር የሚፈጀውን ጊዜ ከሁለት ቀን ወደ ሁለት ሰአት እንደሚቀንስ እና ለኤምዲአር ቲቢን ለመመርመር የሚፈጀውን ጊዜ ደግሞ ከሁለት ወር ወደ ሁለት ሰአት እንደሚቀንስም ነው መግለጫው ያመለከተው።

በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ሀላፊ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን 126 የጄኔክስፐርት ማሽኖችን ለኢትዮጵያ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በቅዱስ ጴጥሮስ የቲቢ ሆስፒታል አርብ ጥቅምት 25 ቀን ድጋፉን አስረክበዋል።

መግለጫው አንደሚያመላክተው ከሆነ ኢትዮጵያ የሳንባ ነቀርሳ እና የቲቢ/ኤችአይቪ በጋራ የሚያዙ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር ካለባቸው 30 ሀገራት ተርታ ትሰለፋለች። በፈረንጆቹ 2021 ብቻ 19,000 ሰዎች በቲቢ የሞቱ ሲሆን ይህም በየቀኑ በየሰዓቱ ወደ ሶስት የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ወገኖች በቲቢ ሕይወታቸው የሚያልፍ መሆኑን ያሳያል።

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ማሽኖቹን ሲቀበሉ “ከዩኤስኤአይዲ እየተቀበልናቸው ያሉት ማሽኖች በሀገሪቱ ፈጣን የሞለኪውላር ቲቢ ምርመራ ተደራሽነት አንዲኖርና በጤና ተቋማቱ ያለውን ክፍተት ለማጥበብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል” ብለዋል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.