አዲስ አበባ መስከረም 30 ዓ/ም – የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋራቢስታን በሚገኘው የጅቡቲ ጦር ታጁራህ ክፍለ ጦር ላይ የታጠቁ ሃይሎች ያደረሱትን ጥቃት አውግዘዋል። ኢጋድ ድርጊቱን አውግዞ “የወንጀለኛና ፈሪ” ጥቃት ነው ሲል ኮንኖታል።
የጅቡቲ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ቅዳሜ መስከረም 26 ቀን ታጣቂዎቹ የሃገሪቷ ወታደሮች ላይ ባደረሱት ጥቃት ሰባት ወታደሮችን ገድለዉ፤ አራት ሲያቆስሉ ሌሎች ስድስት ወታደሮች እስካሁን የት እንዳሉ አይታወቅም።
ሚኒስቴሩ ለጥቃቱ ተጠያቂው የአፋር ህዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ በሚል ራሱን አንድነትና ዴሞክራሲ አስመላሽ ግምባር (FRUD) ብሎ የሚጠራ የአማጺ ቡድን ነው ሲሉ አስታውቀዋል።
ሚኒስቴሩ አንዳሉት ከሆነ “በሃገሪቱ ዋና ዋና የተባሉ ቦታዎች የሚገኙ ሰዎችን በማሸበር እና በመዝረፍ አጸያፊ እና የወንጀል ድርጊቶችን ፈጽሟል ሲል ከሰዋል። “አጋዥ ሃይል ወደ ቦታው የተላከ ሲሆን ጉዳዩ በቅርብ ክትትል እየተደረገበት ነው” ብለዋል።
የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጊሌ በበኩላቸው “እነዚህ ሁሉ ወንጀለኞች በህግ እንደሚጠየቁ፣ እንዲታሰሩ እና ለፍርድ እንደሚቀርቡ” አስረግጦ ተናግረዋል።
“ጅቡቲ የሰላም መናኸሪያ በመሆኗ በአካባቢው ሰላም አብሮ ለመኖር ትልቅ ሚና ትጫወታለች” ብለዋል ዶ/ር ወርቅነህ። “ይህን የወንጀል ድርጊት የፈጸሙ ሰዎች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው” ብለዋል። አስ