ዜና፦አሜሪካን ሀገር የሚኖሩ የጎንደርና አካባቢዋ ተወላጅ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በጦርነት ለወደሙ በዋግ ኽምራ አካባቢ ለሚገኙ የቅዳሚት 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 150 የመማሪያ ኮንባይን ዴስክ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፡ህዳር 5/2015 ዓ/ም፦ በአሜሪካ ሀገር የሚኖሩ የጎንደርና አካባቢዋ ተወላጅ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን 900ዐዐዐ ብር ወጭ የተሰራ የተማሪ መማሪያ 150 ኮምባይን ዴስክ በተወካዮቻቸው አማካኝነት አስረክበዋል። በዋግ ልማት ማህበር (ዋልማ) አስተባባሪነት የመጣው ድጋፍ ለማጓጓዢያ ወጭ 80000 ብር የሸፈነ ሲሆን ከክልሉ ትምህርት ቢሮ የማጓጓዢያ ተሸከርካሪና የኮምበባይን ዴስክ ማሰሪያን ጨምሮ ጠቅላላ ወደ 980 ሺህ ብር ወጭ ሸፍኗል።

የዲያስፖራ ተወካዮች፣ ቤተሰቦች፣ የዋግ ልማት ማህበር፣ ስራ አስኪያጅና ባለሙያዎች፣ የዝቋላ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት ተወካዮችና የሚመለከታቸው በተገኙበት አጠቃላይ ወጭ አንደ ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ወጭ የሸፈነው ኮምባይን ዴስክ በቅዳሚት 1ኛ ደረጃ ት/ምርት ቤት በመመደብ ርክክብ ተካሒዷል።

የተማሪ መማሪያ ኮምባይን ዴስክ ዴያስፖራዎችን በማነጋገር በዋግ ልማት ማህበር አስተባባሪነት የተገኘ ድጋፍ ሲሆን ከጎንደር አስከ ዋግ ኽምራ ያለውን የትራንስፖርት ወጭ እስከ 80000 ሺህ ብር ሸፍናል።
የጎንደር ከተማ ነዋሪና የዲያስፖራ ተወካይ አቶ አብልኝ ሙሉ ድጋፋን በአስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት አካባቢው በተደጋጋሚ በጦርነት የወደመ አካባቢ በመሆኑ በተለያዬ የድጋፍ አይነት በጎንደርና አካባቢዋ ዲያስፖራ አባላት አማካኝነት ከደጀንነት ጀምሮ ኮምባይን ዴስኩን ጨምሮ የተለያዬ ድጋፍ መደረጉን አስታውሰዋል።

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ትምህር መምሪያ ተወካይ አቶ ወንድሙ አየነው በበኩላቸው በጦርነት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ከወደሙት 94 ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ በሆነው በዝቋላ ወረዳ ለሚገኘው ቅዳሚት 1ኛ ደረጃ ት/ ቤት የሚሆን 150 የመማሪያ ኮምባይን ዴስክ ድጋፍ መደረጉ በዚህ ወሳኝ ስዓት ትልቅ አስተዋፅኦ መሆኑን ተናግረዋል።
አንድ ኮምባይን ዴስክ ለ 3 ተማሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ ሆኑ የአለው አንገብገጋቢ ችግር በመገንዘብ የ150 ኮምባይን ዴስክ ድጋፍ 450 ተማሪዎችን እንደሚያስተናግድ አቶ ወንድሙ አየነው ጨምረው አስተውቀዋል።
የዝቋላ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ተወካይ አቶ ታረቀኝ ተስፋዬ በበኩላቸው የቅዳሚት 1 ደረጃ ትም/ት ሙሉ ለሙ ከወደሙት አንዱና እስከአሁን የመማር ማስተማሩ እንቅስቃሴ ያልጀመረ መሆኑን በመረዳት በዚህ ስዓት ድጋፍ መደረጉን አመስግነዋል።

የዋግ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አምላኩ አበበ እነደገለፁት የዋግ ኽምራና አካባቢው በጦርነቱ ምክንያት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስን በማስከተል ችግሩ ውስብስ እንዲሆን አድርጎታይህን በመገንዘብ ዲያስፖራና በጎ አድራጊ ኢትዮጵያዊያን ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የጥሪ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመጨረሻም በአሜሪካ የሚኖሩ የጎንደርና አካባቢዋ ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራ አባላት ወገን ህዝባቸውን ለመታደግ ለአደረጉት ተከታታይ ልዩ ልዩ የድጋፍ አስተዋፅኦ በዋግ ኽምራ ህዝብና በልማት ማህበሩ ስም የተዘጋጀውን ምስጋናና ምስክር ወረቀት ከብሔረሰብ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ እና ከዝቋላ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ተወካዮች እጅ ተረክበዋል። ዋግ ኽምራ ኮሙዩኒኬሽን
No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.