ዜና፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከቀረቡበት ሶስት ተደራራቢ ክሶች ዉስጥ ከሁለቱ ነፃ ነው ሲል ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

በብሩክ አለሙ @Birukalemu21

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14/2015 ዓ.ም፡- የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዓቃቢ ህግ በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ ካቀረበበት ሶስት ተደራራቢ ክሶች ውስጥ 1ኛ እና 2ኛ ክስን በተመለከተ ያቀረበው ማስረጃ ወንጀሉን የሚያስረዳ ሆኖ ስላላገኘው ክሱን ውድቅ እንደረገውና 3ኛውን ክስ ብቻ እንዲከላከል ብይን መስጠቱን ጠበቃው አቶ ሄኖክ አክሊሉ ቕዳሜ ጥቅምት 12 ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ፡፡

የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህግ መንግስት እና የሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የፍትሕ መጽሔት ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከቀረበበት ሶስት ክሶች ውስጥ ከሁለቱ ክሶች ነፃ ነው ሲል ብይን የሰጠው አርብ ጥቅምት 11 በዋለው ችሎት መሆኑን ጠበቃው አቶ ሄኖክ ጨምረው አብራርተዋል፡፡

ተመስገን ተከሶበት የነበረው 3ኛውን ክስ በተመለከተም፤ ፍርድ ቤቱ “በማነሳሳትና በመገፋፋት የወንጀል ተግባር ፈጽሟል” ተብሎ ቀርቦበት የነበረውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 44 (1) 2) እና 257 (ሠ) የመረመረ ሲሆን “ተከሳሹ መከላከል ያለበት ዓቃቢ ህግ ባቀረበው የክስ አንቀፅ ሳይሆን በጥላቻ ንግግር አዋጅ ስር ባለው መሆን አለበት” በማለት የጥላቻ ንግግር ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ 1185/2012 እንዲከላከል በአብላጫ ድምጽ ብይን ሰጥቷል ብለዋል ጠበቃው፡፡

በብይኑ ላይ ሁለቱ ዳኞች ተመሳሳይ አቋም የነበራቸው ሲሆን አንዳኛው ዳኛ ግን ጋዜጠኛ ተመስገን በሶስቱም ክሶች ሊከላከል ይገባል የሚል የልዩነት ሀሳብ ነበራቸው ሲሉ አቶ ሄኖክ ተናግረዋል።

ጋዜጠኛው አሉኝ የሚላቸው ማስረጃዎች ካሉ ለህዳር 2 እና 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ለፍርድ ቤቱ አቅርቦ እንዲያሰማ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ  “ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት፣ ህዝቡ በመከላከያ ሰራዊት ላይ እንዲሁም በመንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ እና እንዲያምፅ በመቀስቀስ” ጠርጥሬዋለሁ ሲል ፖሊስ ሀሙስ ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓም ረፋድ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወቃል።

ፌዴራል ዐቃቤ ህግ  በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ ሰኔ 22፣ 2014 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የህግ መንግስት እና የሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሶስት ተደራራቢ የወንጀል ክሶች መመስረቱ ይታወቃል። ክሶቹም “የአገር መከላከያ ሚስጥር በማውጣት”፣ “በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የሀሰት ወይንም የሚያደናግር መረጃ በማውጣት”፣ “ወንጀል በማነሳሳትና በመገፋፋት” የሚሉ ነበሩ።

በሰኔ 7፤ 2014 ችሎት ላይ ዐቃቤ ህግ ተመስገንን “ወታደራዊ ምስጢሮችን ለማይመለከተው አካል በግልጽ በመጻፍ” ወንጀል እንደጠረጠረው ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። ከዚህ በተጨማሪም “የተቋሙን እና የሰራዊቱን መልካም ስምና ተግባር በማጥፋት” ፣ እንዲሁም “የሰራዊቱን ሞራል ለበማሳነስ በተቀናጀ ዘዴ” በመንቀሳቀስ መጠርጠሩን ገልጾ ነበር። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.