ዜና፡ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ዋስትና መብት ታገደ

በማህሌት ፋሲል

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 1፣ 2014 ዓ.ም ፦“የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የዋስትና መብት ተከለከለ” ሲሉ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።

ትናንት ሰኔ 30 ቀን የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ፀረ ሽብር ምድብ ችሎት ባስቻለው ችሎት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የፍትሕ መጽሔት ባለቤት እና ማኔጂንግ ዳሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የዋስትና ብይን በፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የታገደ ስለሆነ ጋዜጠኛው ከእስር እንደማይፈታ ማስረዳቱን የጋዜጠኛው ጠበቃ በተጨማሪ ተናግረዋል።

ጠበቃ ሄኖክ እንዳሉት ችሎቱ ጋዜጠኛው ያልተፈታበትን ይሄን የጠቅላይ ፍ/ቤት ምክንያት የተቀበለው ሲሆን ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው “ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ በዋስትና ሊፈታ አይገባም” ክርክር ላይ ይግባኙን ለማድመጥ ለሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ/ም ቀጠሮ እንደያዘም ጠበቃው አክለው ተናግረዋል።

ሰኔ 27 ቀን፣ 2014 ዓ.ም፣ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስት ጉዳዩች እና የፀረ ሽብር ችሎት የቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በተከሰሰበት ሶስት የወንጀል ክሶች ማለትም 1ኛ ክስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 44(1)፣ (2) እና 336(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ የአገር መከላከያ ሚስጥርን በማውጣት ሲሆን 2ኛ ክስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 44(1)፣ (2) እና 337(1) ስር የተመለከተውን በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የሚያደናግር ወይም የሀሰት መረጃ በመተላለፍ እና 3ኛ ክስ በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 44(1)፣ (2) እና 257(ሠ) ስር የተመለከተውን ወንጀል በማነሳሳት እና በመገፋፋት የሚል  3 ተደራራቢ ክስ የተከሰሰ እንደነበር ይታወሳል።

ቢሆንም በሰኔ 27 ቀን፣ 2014 ዓ.ም፣ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስት ጉዳዩች እና የፀረ ሽብር ችሎት የቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በተከሰሰበት ሶስት የወንጀል ክሶች በ100,000 ብር ዋስ ከእስር እንዲወጣ የዋስትና መብት መፈቀዱ ይታወሳል።

ዋስትናው በሁለት ዳኞች ፍቃድ እና በአንድ ዳኛ ተቃውሞ ባብላጫ ድምጽ ተፈቅዷል። በዚህም መሰረት በጋዜጠኛ ተመስገን ላይ የቀረበው ክስ መቃወሚያ ጠበቆች በጹሁፍ ለሃምሌ 11 2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ  ”ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት፣ህዝቡ በመከላከያ ሰራዊት ላይ እንዲሁም በመንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ እና እንዲያምፅ በመንቀሰቀስ” ጠርጥሬዋለው ሲል ፖሊስ ሀሙስ ግንቦት 18 ረፋድ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወቃል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.