ዜና፡ የዘገየዉ በአፍሪካ ህብረት የሚመራዉ የኢትዮጵያ የሰላም ድርድር ከአራት ቀናት በኃላ በደቡብ አፍሪካ አንደሚካሄድ ተገለጸ

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ። ፎቶ፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ጥቅምት 10/ 2015: የጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን “የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሚመራዉ የሰላም ድርድር በደቡብ አፍሪካ ጥቅምት 14 ቀን 2015 ዓ.ም አንደሚደረግ አሳውቆናል” ሲሉ ገለፁ።

መስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም አፍሪካ ህብረት ለትግራዩ መሪ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በፃፈዉ ዳብዳቤ ጥቅምት 29 2015 ዓ/ም አሁድ በደቡብ አፍሪካ ሊደረግ ታቅዶ በነበረዉ የሰላም ድርድር አንዲሳተፉ መጋበዙ ይታወሳል። ተመሳሳይ ጥሪ ለፈዴራሉ መንግስትም የቀረበ ሲሆን ሁለቱም አካላት የቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው ነበር።

ሆኖም በሁለቱም በኩል ሊደረግ የታቀደው የሰላም ድርድር በሎጅስቲክ ምክንያት መዘግየቱ ተገልጧል፡፡

የሰላም ድርድር ተሳታፊ ተብለው የተሰየሙት የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በድርድሩ ላይ መገኘት እንደማይችሉ ገልፀው በድርድሩ አካሄድ ላይ ግልፅ መረጃ  እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ድርድሩን ጥርጣሬ ውስጥ አስገብቶት ነበር፡፡

የፌደራል መንግስት ድጋሜ በድርድሩ ላይ ለመሳተፍ ቁርጠኝ ነው ሲሉ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ ጠዋት በትዊተር ገፃቸው ገልፀዋል። አክለውም  የሰላም ድርድሩ ፍሬያማ አይሆንም በማለት የሀሰት ወሬ የሚነዙ አካልት እንዳሳሰቧቸው ገልፀዋል፡፡

አፍሪካ ህብረት ይካሄዳል በተባለው የድርድር  ሂደት ላይ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.