ዜና፡ የማላዊ ፖሊስ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሊሆን ይችላል የተባለ የጅምላ መቃብር ማግኘቱ ተገለፀ

ፎቶ፡ ማላዊ24

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 10/ 2015 ዓ.ም፡- የማላዊ ፖሊስ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሊሆን ይችላል ያለውን 25 አስከሬን የያዘ የጅምላ መቃብር ማግኘቱን የማላዊ መገናኛ ብዙሃን የአከባቢውን ፖሊስ ዋቢ አድርጎ ዘገበ፡፡

“መቃብሩ የተገኘው ማክሰኞ ረፋድ ላይ ቢሆንም አስክሬኖቹን ማውጣት የጀመርነው ዛሬ ነው። እስካሁን 25 አስከሬኖች አግኝተናል” ሲል የፖሊስ ቃል አቀባይ ፒተር ካላያን መግለፁን AFP ዘግቧል። 

እንደ ሪፖርቶቹ ከሆነ ፖሊስ ሟቾቹ በማላዊ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ እየተጓዙ እንደነበር ግምቱን ገልጧል። ከማላዊ ዋና ከተማ ሊሎንግዌ በስተሰሜን 250 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ምዚምባ አካባቢ ያሉ የአካባቢው ሰዎች ከአንድ ወር ያነሰ ጊዜ እንደቆየ ስለሚገመተው የጅምላ መቃብር ለአካባቢው ፖሊስ አሳውቀዋል።

እንደ ማላዊ24 ዘገባ የሰሜን ክልል ፖሊስ ከጥር እስከ መስከረም ባለው ጊዜ ውስጥ 221 ስደተኞችን መያዙን ገልጿል፤ ከነዚህም ውስጥ 186ቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ፖሊስ ጉዳዩን እየመረመርኩ ነው ብሏል።

ባሳለፍነው አመት ሰኔ ወር ላይ አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በመሆን ባደረጉት ማጣራት በማላዊ የነበሩ ከ500 በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው የመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው የጉዞ ሰነድ በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተሰጥቷቸዋል።

የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት እንደገለፀው ማላዊ ወደ ደቡብ አፍሪካ በሚወስደው የየብስ መስመር ላይ የምትገኝ የመተላለፊያ ሀገር ስትሆን ብዙ ጊዜ ‘ደቡባዊ መስመር’ በመባል ትታወቃለች። መንገዱን በዋናነት ከኢትዮጵያ እና ከሶማሊያ የመጡ ያልተመዘገቡ ስደተኞች እስከ ኬፕታውን ድረስ የስራ እድል ለማግኘት ይጠቀሙበታል። በመሆኑም ደቡብ አፍሪካ ከመግባታቸው በፊት በታንዛኒያ፣ ማላዊ፣ ዛምቢያ፣ ዚምባብዌ ወይም ሞዛምቢክ ማለፍ አለባቸው።

የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በግንቦት ወር ይፋ ባደረገው ጥናት ‘ደቡባዊ መስመር’ በረጅም ርቀት ጉዞ፣ በርካታ ድንበር ማቋረጥ፣ በደላሎች ላይ ያለው እምነት በመቀያየር ምክንያት ከፍተኛ የደህንነት ስጋቶች የተሞላበት መሆኑን ገልጧል።

በ2008 ዓ.ም.  ድንበር የለሽ ዶክተሮች እንደገለፀው  አብዛኛዎቹ  ከኢትዮጵያ የመጡ ከ200 የሚበልጡ ስደተኞች ፤ ህጋዊ ሰነድ ስለሌላቸው በአሁን ጊዜ በማላዊ እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ። “አብዛኞቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጓዝ ላይ ነበሩ” ሲል የህክምና በጎ አድራጎት ድርጅቱ ገልጿል። ስደተኞቹ አብዛኛውን  ጊዜ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ታስረው ይቆያሉአስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.