ዜና፡ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ያውጠው መግለጫ ሙስሊሙን ማህበረሰብ የማይመጥን በመሆኑ አንቀበለውም ሲል የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አስታወቀ

በሚሊዮን በየነ @MillionBeyene

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25/2015 ዓ.ም፡- የኦሮምያ ክልል መንግስት በክልሉ እየተከናወነ ያለው ህገ-ወጥ ግንባታን ማፍረስ ተግባር በመስጂድና ሸገር ከተማ ላይ ብቻ ያተኮረ አለመሆኑንና በህገ-መንግስቱ እና በህግ አግባብ መሰረት በክልሉ ከ600 በላይ ከተማዎች ላይ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን በኮሙዩኒኬሽን ቢሮው በኩል ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ.ም መግለጹ ይታወሳል። በተጨማሪም የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ ሀይማኖትን ሽፋን በማድረግ መንግስት በመስጂዶች ላይ ብቻ እንዳነጣጠረ አድርገው ፕሮፓጋንዳ የሚነዙ ፅንፈኞችን  እንዲቃሙ በማሳሰብ ተቋማቱ  የሃይማኖት ሽፋን  በማድረግ የሀገሪቱን ሰላምና መረጋጋት ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ አካላትን አደብ እንዲያስገዙ ጥሪ አቅርቧል።

ይህንን ተከትሎ በትላንትናው ዕለት መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን የሰጠው መግለጫ ሙስሊሙን ማህበረሰብ የማይመጥን ሲለ በመተቸት እንደማይቀበለው ትላነት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የመስጊድ ፈረሳውን በተመለከተ የፌደራሉ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ከኦሮሚያ እና ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክርቤት የተውጣጡ 9 አባላት ያሉት ኮሚቴ በማዋቀር ጉዳዩን እየመረመረ እንደሚገኝ መግለጫው ጠቁሟል። በተዋቀረው ኮሚቴ አማካኝነት ከፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር እየተወያየ መሆኑን ያስታወቀው መግለጫው የተጀመረው ውይይት እልባት እስከሚያገኝ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በትእግስት እንዲጠባበቅ አሳስቧል። የመስጂዶች መፍረስን ለፖለቲካ አላማቸው መጠቀሚያ ለማድረግ የሚሞክሩ አካላት አሉ ሲል ያመላከተው መግለጫው ህዝበ ሙስሊሙ ይህንን በመገንዘብ ሁኔታውን በመጥፎ ጎኑ እንዳይጠቀሙበት ሰላሙን አጠናክሮ የጠቅላይ ም/ቤታችንን ውሳኔ እንዲጠባበቅ ጠይቋል።

በተያያዘ ዜና ከአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ፌስቡክ ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት የከተማዋ ህዝበ ሙስሊም የዛሬ ግነቦተ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጁመዐ በሰላም እንዲያሳልፍ ጥሪ አስተላለፏል። ህዝበ ሙስሊሙ ከዚህ ቀደም ሀይማኖታዊ መብቱን ለማስከበር ባለፈ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ቀድሞ የነበረውን አምባገነን ስርአት ለመለወጥ ፊት-አውራሪ በመሆን ታግሏል ሲል ገልጿል።

የስረአት ለውጥ ከተስተዋለ ወዲህ በተለይ በጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ የሚመራው መንግስት ለህዝበ ሙስሊሙ የሚገጁ በረካታ ምላሾች ሰጥቷል ሲል አወድሷል።

በመንግስት እየተሰጡ ያሉ በጎ ምላሾች ያላስደሰታቸው በእምነቱ ላይ የውስጥ ጥላቻ ያነገቡ፣የግል ፍላጎት ያላቸው፣ድብቅ የፖለቲካ አስተሳሰባቸውን ለማሳካት እንዲሁም ሙስሊሙ ማህበረሰብ ተጠቃሚነቱ ከጎላ ፣ሰላሙን ከተጎናፀፈ ማየትን የማይችሉ መስማትን የማይወድ ፣አካላት ሌት ተቀን በመስራት ማህበረሰባችንን ከመንግስት ለመነጠል እየሰሩ ይገኛሉ ሲል ተችቷል።

መንግስትም ጉዳዩን በፍጥነት እልባት እንዲሰጥ እና ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ከእስር እንዲፈታ ጠይቋል።

በሌላ ዜና በአሜሪካ በእስልምና ጉዳዮች ዙሪያ የሚንቀሳቀሰው The Council on American-Islamic Relations (CAIR) የተሰኘ ድርጅት የባይደን አስተዳደር የኢትዮጵያ መንግስት የሚያካሂደውን የመስጊድ ፈረሳ ለማስቆም ወሳኝ እርምጃዎች እንዲወስድ የሚጠይቅ መግለጫ አወጥቷል። በኦሮምያ ክልል ሸገር ከተማ 19 መስጊዶቸ መፈረሳቸውን እና ከዚሁ ጋር በተያያዘም ሁለተ ሰዎቸ መሞታቸውን የኢትዮጵያ እልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ያወጣውን መረጃ በዋቢነት አስቀምጧል። ኢትዮጵያ ሙስሊሞችን በመጠበቅ የቆየ ባህል ያላት ሀገር ናት፤ አሁን በተፈጠረው ሁኔታ ሳቢያ ይህ ታላቅ ባህል መበረዙ የሚያሳፍር ነው ሲሉ የድርጅቱ ምክትል ሃላፊ ኤድዋርድ አህመድ ሚሸል መግለጻቸውን አስታውቋል። የባይደን አስተዳደር የመስጊድ ፈረሳውን ለማስቆም አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድም ሃላፊው ጠይቀዋል።

መንግስት በኦሮምያ እና አዲስ አበባ በእስልምና ዕምነት ተቋማት ላይ እየፈጸመ ያለው የመስጊድ ፈረሳና በዕምነቱ ተከታዮች ላይ እየፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እንዲቆሙ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ መጠየቁን መዘገባችን ይታወሳል። ይህ የቤትና የዕምነት ተቋማት የፈረሳ እንቅስቃሴ ህዝቡን በማወያየትና ተተኪ ቦታ በመስጠት መከናወን የሚገባው ድርጊት ሆኖ ሳለ የአፈጻጸም ክፍተት ባለበት ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል ሲል የሰብአዊ መብቶች ጉባኤው ኮንኗል፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.