ዜና፡ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ባቀረበችው የሶስት ወር እግድ አቤቱታ ላይ ፍርድ ቤቱ ዛሬ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1 / 2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ  ቤተክርስቲያን ህገ ወጥ የሆነ ሹመት ሰጥተዋል በተባሉት በአቡነ ሳውሮስና በ25 ቱ ተሻሙዎች እንዲሁም ህግ የማስከበር ግዴታቸውን አልተወጡም ባለቻቸው የኦሮሚያ ክልል መንግስት፣የፌደራል ፖሊስና የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽኖች ላይ ባቀረበችው የዕግድ አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለዛሬ የካቲት 1 ቀን 2015 ዓም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ  ቤተክርስቲያን ጠ/ሚንስትሩን ጨምሮ የፀጥታ ሃይሎች ከድርጊቱ እንዲቆጠቡ ቤተ ክርስቲያኗ የሚመለከተው አካል ትዕዛዝ እንዲሰጥ እንደምትፈልግ ለልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሠረታዊ መብቶች ችሎት የሕግ ባለሞያዎቿ ማስረዳታቸውን ቋሚ ኮሚቴው በሰጠው መግለጫ ገልጧል፡፡

ችሎቱ የሃይማኖት ጉዳይን ተመለከተ ምን አይነት ትእዛዝ እንዲሰጥ ትፈልጋላችሁ ተብሎ ደኞች ለጠየቁት ጥያቄ ጉዳዩ አንድ በሁለት የተለያየ ሀይማኖት ውስጥ ባሉ አካላት ሳይሆን በአንድ ሀይማኖት ውስጥ የነበሩ ነገር ግን አሁን በተገለሉ ሁለት ቡድኖች መካከል መሆኑን አስረድተናል ሲሉ ጠበቃ አንዷለም በውቀቱ ገልፀዋል፡፡

እግድ የጠቀቃችሁት ምን አይነት ክስ ለመመስረት ነው ተብለን ለተቀየቅንው የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ካላት ምእመን፣ የቤተ ክርስቲያን ብዛት አንፃር በቂ ጊዜ ወስደን ሰፋ ያለ ክስ ማዘጋጀት ለማዘጃገት የሶስት ወር እግድ መጠየቅ አስፈላጊ መሆኑን አስረድተናል ሲል አንዷለም ገልፀዋል፡፡

ችሎቱ ማብራሪያውን ከሰማ በኋላ ሶስቱ ዳኞች መነጋገር ስለሚኖርባቸው ለዛሬ የካቲት 1 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ብለዋል፡፡

ጥር 28 በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ልዩ ዞን ድንበር በተለምዶ ፊሊዶሮ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቅድስት ለደታ ቤተ ክርስቲያን የተሰበሰቡ ሰዎች “የታሰሩ ሰዎች ይፈቱ” በማለት መንገድ በመዝጋት የፀጥታ ችግር ኢንዲከሰት በማድረግ በ19 ፖሊሶች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ማድረሳቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቋል፡፡

በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሻሸመኔ ከተማ  ቅዳሜ ጥር 27 በኦርቶዶክስ ምዕመናን እና በከተማ ፖሊስ መካካል በተነሳ ግጭት የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን የአይን እማኝ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፀ፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰው በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በአዲሱ “የኦሮሚያና ብሔሮች ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ” የተሾሙ አባላት የአቀባበል ሥነ ሥርዓት ላይ በነበረበት ወቅት ነው።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንና በፌዴራል መንግስት መካከል እየተፈጠረ ያለው እሰጣገባ በኦሮምያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በሶዶ ዳጬ ወረዳ በወሊሶ ከተማ በበአለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን በአቡነ ሰውሮስ እና ሌሎች ሁለት ጳጳሳት መሪነት በርካት ህዝበ ክርስቲያንን ያስቆጣው የ26 ጳጳሳትን ከቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቀኖና ውጭ መሾማቸውን እንዲሁም መወገዛቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ መንግስት በጉዳዩ ላይ  እጁን በማስገባቱ ከሷል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.