አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5/2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቀጣይ ሳምንት ግንቦት 8 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አትላንታ ጆርጂያ የቀጥታ በረራ እንደሚጀምር ተገለጸ። የአትላንታ ከተማ ከንቲባ አንድሪ ዲከንስ በረራውን ለማስጀመር ወደ አዲስ አበባ ማቅናታቸውን የከተማዋ መገናኛ ብዙሃን የአትላንታ ከንቲባ ጽ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫን ዋቢ በማድረግ አስታውቀዋል። አየር መንገዱ በሳምንት አራት በረራዎችን እንደሚያደርግ ዘገባዎቹ ጠቁመዋል።
አትላንታ እና አዲስ አበባ አለም አቀፍ ከተሞች ናቸው፤ ሁለቱም የባህል አና የኢኮኖሚ ትስስር ያላቸውን ከተሞች ይበልጥ በንግድ፣ ቱሪዝም እና ባህል ለማቀራረብ የቀጥታ የንግድ በረራ መጀመሩን ሳበስር በደስታ ነው ሲሉ ከንቲባው መናገራቸውንም አስታውቀዋል። አትላንታ የአሜሪካን መግቢያ በር ሁና እንደምታገለግለው ሁሉ አዲስ አበባም አትላንታ ከአፍሪካ ጋር ለምታደርገው ግንኙነት ተጨማሪ የመግቢያ በር ሁና እንደምታገለግል ያላቸውን እምነት መግለጻቸውንም ዘገባዎቹ አመላክተዋል። ከንቲባው በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከመንግስት ባለስልጣናት፣ ከባለሀብቶች፣ የትምህርት እና የባህል መሪዎች ጋር እንደሚገናኙ ዘገባዎቹ አካተዋል። አስ