አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14/2015 በፈረንሳይ ፓሪስ በተካሄደው የ2023 ስካይትራክስ የአየር መንገዶች ሽልማት ስነስርዓት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአምስት የተለያዩ ዘርፎች የክብር ሽልማቶች ማግኘቱን አየር መንገዱ በማህበራዊ ሚዲያ ፌስቡክ ገጹ ይፋ ያደረገው መረጃ አመላከተ።
ዘንድሮም አየር መንገዱ ለተከታታይ ስድስተኛ ዓመት ‘ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ’ በሚል ዘርፍ ተሸላሚ በመሆን ክብሩን ማስጠበቁን አስታውቋል።
በምርጥ ቢዝነስ እና ኢኮኖሚ ክላስ ኤርላይን ዘርፍ ለአምስተኛ ጊዜ መሸለሙን ያስታወቀው አየር መንገዱ የአመቱ የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክላስ የአየር ላይ የምግብ እና መጠጥ መስተንግዶ በማቅረብ እና የአመቱ ጽዱ የአፍሪካ አየር መንገድ በሚል ዘርፍም ሽልማት ማግኘቱን ጠቁሟል።