ዜና፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ገለልተኛ መርማሪዎችና መገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ወደ አማራ ክልል እንዲገቡ በአስቸኳይ እንዲፈቅድ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13/ 2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ መንግሥት ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት መርማሪ ባለሙያዎች ኮሚሽን እና መገናኛ ብዙኀን የግጭት ቀጠና ወደሆነው አማራ ክልል እንዲገቡ ባስቸኳይ እንዲፈቅድ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።

አምነስቲ ትላንት ባወጣው መግለጫ በክልሉ በተፈጸሙ የአየር ጥቃቶች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል ሲል ጠቅሶ በፍኖተሰላም፣ ባሕርዳርና ሸዋሮቢት የጅምላ ግድያዎች መፈፀማቸውን መረጄዎች ደርሰውኛል ብሏል፡፡

“በመሆኑም ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት መርማሪ ባለሙያዎች ኮሚሽን እና መገናኛ ብዙሀን ወደ ክልሉ ገብተው ምርመራ እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ መንግስት መፍቀድ አለበት” ሲሉ  የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ቲጌሬ ቻጉታህ ገልፀዋል፡፡

አክለውም መንግሥትና ጸጥታ ኃይሎች ሰብዓዊ መብቶችን መጠበቅና ማክበር አለባቸው ሲሉ ቲጌሬ አሳስበዋል፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.