አዲስ አበባ፣ ህዳር 10/2015 ዓ.ም: – የቀድሞው የሶማሊ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ሲራጅ አደም ሐሙስ ህዳር 9 ቀን 2015 ዓ/ም በድሬዳዋ ከተማ ተይዞ ወደ ሶማሊ ክልል መዲና ጅግጅጋ ከተማ ተወስደው በእስር ላይ አንደሚገኙ ለአዲስ ስታንዳርድ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል።
የቀድሞ የሶማሊ ክልል የጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ሲራጅ አደም በ2013 ዓ/ም ከስልጣናቸው ከለቀቁ በኋላ የመንግስት ተቺ በመሆን በተለያዩ ማህበራዊ ድህረ-ገፃቸው ከበርካታ ገለለትኛ ሚድያዎች ቃለ መጠየቅ በማድረግ በክልሉ በሙስና የተዘፈቁ ባለስልጣናትን ሲያጋልጡ ቆይተዋል ሲሉ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት አቶ ሲራጅ አብዲቃድር ገልፀውልናል።
የአቶ ሲራጀ የክልሉ ፖሊስ አባላት መኖሪያ ቤታቸውን ሊፈትሹ መሆኑን ጥቆማ ከደረሳቸው በኋላ፤ በቁጥጥር ሰር ሊውሉ አንደሚችሉ በመስጋት ወደ ድሬዳዋ መሄዳቸውን አቶ ሲራጅ አክለው ገልፀዋል። የክልሉ የፖሊስ አባላት አቶ ሲራጅን ባረፉበት ሆቴል ውስጥ በቁጥጥር ስር ያዋሉት ሐሙስ ማለዳ መሆኑን አቶ ሲራጅ ተናግረዋል።
አቶ ሲራጅ በቀድሞ የክልሉ ፕሬዝዳንት አሁን በአስር ላይ የሚገኙት አብዲ ሞሓመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) ታስሮ አሰቃቂ ነገሮች ደርሶባቸው አንደነበር ኣቶ ሲራጅ ገልፀው አሁንም በጥላቻ ንግግርና ሃሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ተከሰዋል ብለዋል፡፡
አዲስ ስታንዳርድ በጉዳዩ ዙርያ ከሶማሌ ክልል መረጃ ለማግኘት ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም። አስ