አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15/ 2015 ዓ.ም፡- በኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሰደን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ቀጫ ማክሰኞ ሰኔ 13 2015 ዓ.ም በታጣቂዎች መገደላቸውን የወረዳው ኮሚኒኬሽን አስታወቀ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ኮሚኒኬሽን የሰዴን ሶዶ ገለፃ አቶ አስታዳሪው የተደገሉት በአዳማ ከተማ ስብሰባ ተሳትፈው ከተመለሱ በኋላ እሁድ ማታ 3፡00 አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች ኢሉ ወረዳ አስጎሪ ከተማ ከሚገኘው ቤታቸው ተወስደው ማክሰኞ እለት ተገለዋል ሲል ገልጧል፡፡
የምስራብ ሸዋ አስተዳዳሪ የሆኑት ታዬ ጉዲሳ እንደገለፁት አቶ በቀለ በጠላት በወሰደው ጭካኔ በተሞላበት ድርጊት ተገለዋል፡፡ አስተዳዳሪው “የህዝቡን ጥቅም ለማስከበር ቁርጠኛ የሆኑና ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ መሪ” ነበሩ ሲሉም ገልፀዋል።
ይህን በተመለከተ ቢቢሲ በዘገባው ታጣቂዎቹ አቶ በቀለን ከመገደላቸው በፊት እንዲለቀቁ 10 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸውን ምንጮቹን ዋቢ ቸድርጎ ዘግቧል፡፡ የዞኑ የኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ ሃይሉም ታጣቂዎቹ በአስተዳዳሪው ስልክ አንዳንድ ሰዎች ላይ እየደውሉ 10 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸው እንደሰሙ ገልፀዋል ብሏል ዘገባው፡፡
በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ውስጥ ሁለት ሳምንት ባለሞላ ጊዜ ውስጥ የወረዳ አስተዳዳሪ ሲገደል ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ሰኔ 1 ቀን በምዕራብ ሸዋ ዞን የአዳ ባርጋ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አብዲሳ ቀነኒ በበካቴ ከተማ በመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ በታጣቂዎች ተገድለዋል።
በተያዘው አመት በመጋቢት ወር ላይ የነቀምት ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ ደሳለኝ በኮንጃ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች መገደላቸው ይታወሳል፡፡አስ