አዲስ አበባ፣መስከረም 19/2015 ዓ.ም፡- በሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል ወታደራዊ ጦርነት ካገረሸበት ነሃሴ 18 ጀምሮ የሰብዓዊ አገልግሎት አቅርቦት በትግራይ “ሙሉ በሙሉ መታገዱ” ፣ እንዲሁም በአማራ እና በአፋር ክልሎች “እጅግ መስተጓጎሉ”አሳሳቢ መሆኑን የአዉሮፓ ህብረት ገለፀ፡፡ በተጨማሪም ጦርነቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን እንደ አዲስ ማመፈናቀሉ ን እና በሲቪል ንብረቶችና መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ምክኒያት መሆኑን ህብረቱ ገልጧል፡፡
የአዉሮፓ ህብረት የአደጋ ስጋት አስተዳደር ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ላይ የሰብአዊ አገልግሎት ተደራሽነት፣ የነዳጅ እንዲሁም የገንዘብ አቅርቦት በትግራይ “ሙሉ በሙሉ ዝግ” መሆኑን የአዉሮፓ ህብርት ማረጋገጡን አሳዉቋል፡፡ በአማራ እና በአፋር በተጎዱ አካባቢዎችም የሰብዓዊ አገልግሎት ተደራሽነት በእጅጉ ተስተጓጉሏል ብሏል፡፡
የአዉሮፓ ህብረት መግለጫ የወጣዉ የአሜርካ ተራድኦ ድርጅት( USAID) “ሰሜን ኢትዮጵያ” በአለም ላይ ካሉ እጅግ አደገኛ አካባቢዎች አንዱ መሆኑንና ለእርዳታ ሰራተኞች ህይወት አደገኛ ነው ብሎ ከገለፀ ከአንድ ቀን በኋላ ነዉ፡፡
እንደ አዉሮፓ ህብረት የእርዳታ ድርጅቶች ሰራቸዉን አቁመዉ አንዳድ ሰራተኞቻቸዎን ማዉጣት ነበረባቸዉ፡፡ የአዎሮፓ ህብረት የሲቪል ጥበቃ፣የሰብዓዊ ጉዳይ እና የአደጋ ጊዜ ምላሽ አስተባበሪ ጃኔዝ ሌናርቺ “ይህ በሰብዓዊ እርጋታ በሚሊዮን ለሚቆጠሩና በሰብዓዊ እርዳታ ላይ ጥገኛ ለሆኑ በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ለሚገኙ ዜጎች ከባድ ጉዳት ነዉ” ብሏል፡፡
የአዉሮፓ ህብረት የአለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ያወጣዉን ሪፖርት ዋቢ አድርጎ ባወጣዉ መግለጫ “በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች 13 ሚሊዮን ሰዎች በግጭቱ ቀጥተኛ ምክኒያት የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በተመሳሳይ ኢትጵያ ከ1974 ዓ.ም ወዲህ ከተመዘገበዉ እጅግ የከፋ ድርቅ እያጋጠማት ሲሆን በግምት 7.4 ሚሊዮን ዜጎች ለከፋ የምግብ ዋስትና እጦት ተዳርገዋል” ሲል ገልጧል፡፡አስ