አዲስ አበባ፣ ጥር 19/ 2015 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻከል ወረዳ የፀጥታ ኃላፊ አቶ አይናለም አላምነህ እና የወረዳው ሚኒሻ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የነበሩት አቶ አዝመራው አማረ በታጣቂዎች መገደላቸውን የዞኑ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ አስታወቀ።
ኃላፊዎቹ በማቻከል ወረዳ ጥር 27/2015 ዓ.ም. ሌሊት ህዝብን ለማገልገል በነበሩ የጸጥታ አመራሮች ላይ ማንነታቸዉ ባልታወቁ አካላት በተተኮሰ ጥይት ህወታቸዉ መለፉ ገልጿል።
ለህዝብ ሰላም ሲሉ ህዝብን በማገልገል ላይ የነበሩ አካላትን ህይወት የቀጠፉ ወንጀለኞችን የጸጥታ ሃይላችን ከህዝባችን ጋር በመተባበር በአጭር ጊዜ ለህግ ለማቅረብ እንደሚሰራም አስተዳደር ምክር ቤቱ በመግለጫው ገልጿል።
”ለህዝብ ሲባል የሚከፈል መስዋዕትነት ዘላለማዊ ክብር ነው” ያለው የማቻከል ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት ለህዝብ ሰላም ሲሉ መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖችን ሁሌም የሚዘክራቸዉና ቤተሰቦቻቸው የመንከባከብ ኃላፊነትን እንደሚወጣ ምክር ቤቱ አስታዉቋል።