ዜና፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አራት ሚኒስትሮችን “በክብር” ሸኝቷል

አዱስ አበባ፣ ጥር 6/ 2015 ዓ.ም፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም. አራት አባላትን በክብር ሸኝቷል፡፡ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለአራቱም የምክር ቤት አባላት ቀጣይ ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆንላቸው ተመኝቷል ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

አራቱ ሚንስትሮች፣ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ፣ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን እና  የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ተፈሪ ፍቅሬ ናቸው፡፡ ታህሳስ 22 ቀን 2015 ዓ.ም. ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ዑመር ሁሴን እና ተፈሪ ፍቅሬ ቡሳን አምባሳደር አድርገው ሾመዋል።

ወ/ሮ ዳግማዊት እነዲሁም ታከለ ኡማ በሌላ የስራ ድርሻ መሾማቸው እልታወቀም።

በሽኝት መርሐ-ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.