ዜና፡ ፈረንሳይ መንግስት እና የአውሮፓ ህብረት በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል የ32 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበበ፣ ጥር፣ 6/2015 ዓ.ም፡- ፈረንሳይ መንግስት እና የአውሮፓ ህብረት በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል የ32 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ማድረጋቸውን የገንዘብ ሚንስቴር አስታወቀ፡፡

ድጋፉ የተደረገው አዲስ አበባ በሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ ሲሆን የ32 ሚሊዮን ዩሮ የፋይናስ ድጋፉም በግጭት በተጎዱ የአማራ፣ የትግራይ፣ የአፋር፣ የኦሮሚያና የደቡብ ክልሎች የግብርና ምርታማነትን በማሻሻል የምግብ ዋስትናን ለማረጋጋጥ የሚውል ነው ተብሏል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ፈረንሳይ መንግስት እና የአውሮፓ ህብረት በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ሀይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክትን ለማስፈፀም እንዲውል የ10 ሚሊዮን ዩሮ የፋይናስ ድጋፍ አድረገዋል፡፡

የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነቶቹን በኢትዮጵያ በኩል ክብርት ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሲፈርሙ በፈረንሳይ በኩል ደግሞ የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይና የአውሮፓ ሚኒስትር ሚስዝ ካተሪን ኮሎና ፈርመዋል፡፡

የገንዘብ ሚንስትር ደኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው የ10 ሚሊዮን ዩሮ የፋይናስ ድጋፍ ውስጥ ውስጥ 6 ሚሊዮን ዩሮ አዲስ የፋይይናነስ ድጋፍ፣ 4 ሚሊዮን ዩሮ ደግሞ ከዚህ ቀደም ለኤሎክትሪክ ሀይል ማስተላላፊያ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተሰጠውን ብድር ለማራዘም የተደረገ ድጋፍ ነው ብለዋል፡፡

ሳማሪታ በሰጡት ማብራሪያ፣ በፌዴራል መንግስትና በህወሓት አመራሮች መካከል የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ የተለያዩ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ ጉብኝት እያደረጉና ያለንበትን ሁኔታ እያዩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይና የአውሮፓ ሚኒስትር ካተሪን ኮሎና የፈረንሳይ መንግስት 28 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን ገልፀው ቀሪው አራት ሚሊዮን ዩሮ ደግሞ የአውሮፓ ህብረት ድጋፋ ማድረጉን ገልፀዋል፡፡ አክለውም “የተደረገው ድጋፍ ከኢትዮጵያ ጋር ያለንን አጋርነት የሚያጠናክር ነው፡፡ ድጋፉ በግብርና ስራ ላይ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች የሚሰጠው ጥቅም ከፍ ያለ ነው፡፡ ፈረንሳይ እና የአውሮፓ ህብረት ያደረጉት ድጋፍ የኢትዮጵያን ሰላም ዘላቂ እንዲሆን ለማድረግ ጠቃሚ ነው” ብለዋል ካተሪን፡፡

የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪ ኮሎናንና የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ባኤርቦክ  ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ጥር 4/ 2015 ዓ.ም ሲሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የፍትህ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ እና  ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር ተወያይተዋል።

የፈረንሳይ እና የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ከተገናኙ በኋላ ባደረጉት ንግግር በጦርነቱ ወቅት ለተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂነት እንዲኖርም ጥሪ ማቅረባቸው ተዘግቧል፡፡ ሁለቱም ሚኒስትሮች በግጭቱ ወቅት የተፈጸሙ በደሎችን የሚያይ ፍትሃዊ የሽግግር ሥርዓት እንዲመሰረት አሳስበዋልአስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.