ዜና፡ የሀዲያ ዞን ባዴዋቾ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች ባካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ሶስት ሰዎች ላይ ጉዳት መደረሱ ተገለፀ

በአብዲ ቢያንሳ @ABiyenssa

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12/  2015 ዓ.ም፡- የሀዲያ ዞን ምስራቅ ባዴዋቾ ወረዳ ሾኔ ከተማ የመንግስት ሰራተኞች የወር ደመወዝ በጊዜ ስላልተከፈላቸው ባካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ፣ ሰልፉን ለመበተን ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ሶስት ሰዎች ላይ ጥቃት ደርሶ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የወረዳው ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፁ፡፡

ስማቸው እንዲገለፀ ያልፈለጉ በሰልፉ ላይ የተሳተፉት የወረዳው ነዋሪ ላለፉት ሶስት ወራት ለዞኑ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ እናዳልተከፈላቸው ገልፀዋል፡፡ የዞኑ የመንግስት ሰራተኞችም ደመወዝ በወቅቱ የማይከፈላቸው በመሆኑ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደዋል ብለዋል፡፡

ከሰራተኞቹ አንዱ የሆነው ነዋሪው “ ለሆሳዕና ከተማ ሰራተኞች በስተቀር በ 13 ወረዳዎችና ሶስት ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በምዕራብ እና ምስራቅ ባዴዋቾ ወረዳ ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች ለሶስት ወር ደመወዝ ሳይከፈል ቆይቷል” ብሏል፡፡

ከሚያዚያ 13 ማክሰኞ እለት ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የባዴዋቶ ወረዳ ነዋሪዎች በወቅቱ የማይደርሳቸውን የደመወዝ ክፍያ ችግርን በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል፡፡ የሰልፉ ተሳታፊው እንደሚሉት በተካሄደው ሰልፍ ላይ ሰልፈኞቹ የክልሉ መንግስትና የሀዲያ ዞን አስተዳደር ደመወዛቸውን በጊዜ እንዲከፍላቸው ሲጠይቁ ነበር፡፡

“ሰልፈኞቹ ከአዲስ አበባ ወደ አርባ ምንጭ የሚወስደውን መንገድ በመዝጋት የተቃዎሞ ሰልፍ ሲያደርጉ ነበር፤ ነገር ግን ከዛሬ ፖሊሶች መንገዱን አስከፍተዋል” ሲል ተናግሯል፡፡ በዚህም ሂደት ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ሶስት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል ብሏል፡፡ በባዴዋቾ ወረዳ ሾኔ ከተማ ሰልፉን ለመበተን በተደረገ ሂደት አንድ ፖሊስ በራሱ መሳሪያ መጎዳቱንም አክሎ ገልጧል፡፡

እስከካሁን ጥያቄዎቹ ባይመለሱም በአሁኑ ሰዓት ሰልም መስፈኑንና ነዋሪዎች ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.