አዲስ አበባ፣ ህዳር 17/ 2015 ዓ.መ፡- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ተወካይ እና የሰብአዊ እርዳታ አስተባባሪ ዶክተር ካትሪን ሶዚ በትግራይ ያለው የሰብአው እርዳታ አቅርቦት ላይ መሻሻሎች ቢታዩም እርዳታ ከሚያስፈልጋቸ ሰዎች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ወደ ክልሉ የደረሰው የሰብአዊ እርዳታ መጠን በቂ አለመሆኑን ገልፀዋል።
ትናንት በትግራይ ባደረጉት የስራ ጉብኝት በተደጋጋሚ በተፈጠረው ችግር ለሚሰቃዩ ሰዎች ለመድረስ በሁሉም አቅጣጫ በቂ የሰብዓዊ እርዳታ ሊደረግ ይገባል ማለታቸዉን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
በትግራይ የሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም አካል ርብርብ በማድረግ የምግብ፣ የመድሃኒት እና የግብርና ግብአቶች ያለ ምንም ገደብ ወደ ክልሉ እንዲገባ ማድረግ ይኖርብናል ሲሉም አፅንኦት ሰጥተዋል።
በትግራይ ቆይታዋ ሽሬ፣ መቀሌ፣ አይደር እና መቀሌ ሪፈራል ሆስፒታሎችን ጎብኝተዋል።
በኢትዮጵያ መንግስታት እና በክልሉ ባለስልጣናት መካከል የተፈረመው የሰላም ስምምነት ለተቸገሩ ወገኖች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንዲደርስ በር የከፈተ በመሆኑ ሁለቱንም ወገኖች አመስግነዋል።
የስምምነቱን መፈረም ተከትሎ ከህዳር 6 እስከ 12 ብቻ በኢትዮጵያ መንግስት እና ተባባሪ ሰብዓዊ ዕርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች፤ 17,000 ሜትሪክ ቶን ምግብ የጫኑ 435 ማኪኖች እንዲሁም በድምሩ 780 ሜትሪክ ቶን ምግብ ያልሆኑ እና መድሃኒት የጫኑ 19 መኪኖች ትግራይ መግባታቸዉን ተመድ አስታዉቋል።
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ የሰላም ስምምነት መፈራረሙን ተከትሎ ከ2,400 ሜትሪክ ቶን በላይ የምግብ፣ የህክምና፣ የስነ ምግብ እና ሌሎች የህይወት አድን አቅርቦቶችን ለክልሉ ያቀረበዉ የተባበሩት መንግስታት የአለም ምግብ ፕሮግራም እርዳታዉ ከተረጂው ቁጥር አንፃር በቂ እንዳልሆነ ገልጿል።
አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 2.3 ሚሊዮን ችግረኞች በትግራይ መኖራቸውን የገለፀው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ወደ ሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በአፋጣኝ መድረስ እንዳለበትም ገልፅዋል።
የሁለት ዓመታት ግጭት ከ13.6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሰብዓዊ ርዳታ ጠበቂ እንደዳረጋቸው ጠቅሶ ከእነዚህ ውስጥ በትግራይ 5.4 ሚሊዮን (የክልሉ 90 በመቶ) በአማራ 7 ሚሊዮን እና በአፋር 1.2 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል።
በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሰረት በመላው ኢትዮጵያ በድርቅ የተጎዱትን 9.8 ሚሊዮን ዜጎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 22 ሚሊዮን ሰዎች የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ታውቋል። አስ