አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2015 ዓ.ም፡- ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የምግብ ዘይት አንዲያገኝ በጅቡቲ ከሚገኘው ጎልደን አፍሪካ ካምፓኒ የ43,37,412 ሊትር የፓልም የምግብ ዘይት ግዢ መፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስቴር አሰታውቀ፡፡
የግዢ ውሉን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት ሲሆኑ የገንዘብ ሚኒስቴር ለግዢ የሚውለውን የ69 ሚሊዮን 894ሺ 440 የአሜሪካን ዶላር ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋስትና መስጠቱ የገንዘብ ሚንስቴር አስታውቋል፡፡
የምግብ ዘይቱ ግዢ በአንድ አመት የክፍያ ጊዜ የሚፈጸም ነው፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር የግዢ ውሉን ለተፈራራሙት ለኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽንና ለኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅቶች በላከው ደብዳቤ በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ላሉ ሸማቾች የመሸጫ ዋጋ ወስኗል።
በዚህም መሰረት የአዲስ አበባ ባለ 3 ሊትር ምግብ ዘይት መሸጫ ዋጋ 314 ብር ሲሆን ባለ 5 ሊትር 510 ብር እንዲሁም ባለ 20 ሊትር 2003 ብር የሚሸጥ መሆኑ ተገልጧል፡፡
ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ ከተሞችን በተመለከተም ርቀትን ታሳቢ በማድረግ የትራንስፖርት አገልግሎት ክፍያ ታሪፍ በኩንታል 60 ሳንቲም በአንድ ኪ.ሜ መሆኑንን የገለፀው ሚንስቴሩ ይህ ታሳቢ ተደርጎ ሽያጭ እንዲከናወንና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴርም በተለመደው መልኩ የክልልና የከተማ አስተዳደሮችን የስርጭት ኮታ በመመደብ ለኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽንና ለኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት እዲያሳውቅ አቅጣጫ ተቀምጧል ብሏል፡፡
በ2019 በየመናዊው ፉአድ ሃዬል ሰኢድ የሚመራው ጎልደን አፍሪካ ኩባንያ በኢትዮጵያ የምግብ ዘይት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ለማቋቋም አቅዶ የነበረ ሲሆን ተፈፃሚ ሳይሆን ቀርቷል።
ታህሳስ 1፣ 2021 ዓ.ም (አ.አ.አ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ የሀገር ውስጥ ገበያን ለማረጋጋት ባንኮች የውጭ ምንዛሪ እንዲያቀርቡ ቅድሚያ ከተሰጣቸው ዝርዝር ውስጥ የምግብ ዘይት ምርት ግብአት አንዱ ነው።
ነገር ግን፣ የምግብ ዘይት ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በመምጣቱ ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ አምስት ሊትር የምግብ ዘይት በችርቻሮ መደብሮች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ600ብር ወደ 1000 ብር ከፍ ብሎ ነበር ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ መጋቢት 07 ቀን 2022 መሰጡት መግለጫም ፣ ነጋዴዎች ምርቶችን ከማከማቸት እና ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ከማድረግ እንዲታቀቡ አስጠነቅቀው ነበር።አስ