ዜና፡ አሜሪካ ለኢትዮጵያ 55 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ የምግብ ዋስትና ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች

በአማራ ክልል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የምግብ ዋስትና እጦት ተንሰራፍቶ የነበረ ቢሆንም የነበረው ግጭት ሁኔታውን በእጅጉ አባብሶታል። የዩ.ኤስ.ኤ.አይ.ዲ አጋር የዓለም የምግብ ፕሮግራም 650,000 ተፈናቃዮችን እና የማህበረሰብ አባላትን በወርሃዊ የምግብ አከፋፈል እየረዳ ነው። ፎቶ፡ Adrienne Bolen/WFP ግንቦት 2022

ዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 ዓ.ም:- ዛሬ አሜሪካ በዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩኤስኤአይዲ) በኩል ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የምግብ ዋስትና ድጋፍ ወደ 55 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ማድረጓን አስታውቀች።ተቋሙ ባወጣው መግለጫ “ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የምግብ እና የማዳበሪያ ዋጋ በመጨመሩ የምግብ ዋስትና እጦት እያጋጠማት ሲሆን ይህም ሩሲያ በዩክሬን ላይ ባካሄደችው ወረራ በመሆኑ ነው” ብሏል። ዩኤስኤአይዲ ይህንን አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ኢትዮጵያውያን ወቅታዊውን የምግብ ችግር ለመቋቋም እና ወደፊት ከምግብ ጋር የተያያዙ አደጋዎችን ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ ጥንካሬን ለመገንባት ያስችላልም ሲልም ግልጿል።

ይህ አዲስ ኢንቨስትመንት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሰኔ ወር መጨረሻ በጀርመን በቡድን7 የመሪዎች ጉባኤ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለምግብ ዕጥረት ቀውስ ተጋላጭ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች 2 ነጥብ 76 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ እንደምታደርግ በገቡት ቃል መሰረት የተፈፀመ መሆኑም ተነግሯል። .

ይህንን የገንዘብ ድጋፍ በዩክሬን ቀውስ በጣም የተጎዱ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያንን ለማዳረስ ይጠቀማል ያለ ሲሆን፣ ድጋፉ በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭት የውሃ እና መሰል የአቅርቦት ስርአታቸው የወደሙ ገበሬዎችን እንደሚያካትት ተገልጿል። ዩኤስኤአይዲ የውሃ አቅርቦት ስርዓትን መልሶ በመገንባት፣ የግብርና ቢዝነስ ብድር በመስጠት፣ የገበሬ ዩኒየኖችን በማሰልጠን፣ የዘር እና የማዳበሪያ ማከፋፈያ ግንኙነትን  በማጠናከር እና አርሶ አደሮች ወሳኝ የእርሻ መሳሪያዎችን በመግዛት አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያጋጠመውን የምግብ ምርት አቅርቦት ለመቅረፍ ይረዳል ሲልም ግልጿል።

መግለጫው አክሎም በተጨማሪም ተራድዖ ድርጅቱ ከ3 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ የግብርና ቢዝነስ ተቋማት እና በድርቁ ለተጎዱ አርብቶ አደሮችን እና የማኅበረሰቦች ክፍሎችን ለማቋቋም ድጋፉን እንደሚጠቀምበትም አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም በፈንዱ ከ8 ሚሊየን በላይ ሰዎች የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡ በሴፍቲ ኔት ኔት መርሃ ግብር እንዲሁም  ተጠቃሚ እንዲሆኑ ድንበር ዘለል የግብርና ንግድን በእንስሳት ጤና ምርመራ በመሳሰሉ አዳዲስ ተግባራት ለማሻሻል እንደሚሰራም ተመልክቷል፡፡

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.