አዲስ አባባ፤ጥቅምት 15/ 2015 ዓ.ም፡- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው አዲስ መረጃ በዚህ ዓመት ከነሃሴ መጀመሪያ እስከ ጥቅምት ወር ድረስ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በጋምቤላ ክልል 12 ወረዳዎች እና በክልሉ ርዕሰ መዲና በደረሰ የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 185,200 ሰዎች (37,040 አባወራዎች) ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን እና ተጨማሪም 79,631 ሰዎች (15,927 አባወራዎች) መጎዳታቸውን አስታወቀ፡፡
መረጃው የጋምቤላ ክልል የአደጋ ስጋት አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ጋትበል ሙን በነሃሴ ወር በስምንት ወረዳዎች ከ74,000 በላይ ንፁሃን ዜጎች ላይ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል ብለው ካስተላለፉት የተጎጂዎች ቁጥር ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷል፡፡
“የጋምቤላ ክልል ሰፋፊ አካባቢዎች ለተደጋጋሚ የጎርፍ አደጋ የተጋለጡ ናቸው፡፡ ዋናዋናዎቹ ወንዞች አኮቦ፣ አልወሮ፣ ባሮ፣ ጊሎ እና ገባር ወንዞቻቸው ብዙ ዝናብ በሚዘንብበት ጊዜ ሞልተው በመፍሰስ በወንዝ ዳርቻ ያሉ ማህበረሰቦችን በማጥለቅለቅ፣ ውድመትን በመፍጠር፣ ነዋሪዎችን ከቀያቸው በማፈናቀል እና ለውሃ ወለድ በሽታዎች መንስኤ ሆነዋል” ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጧል፡፡
የጎርፍ አደጋው ከሚያዚያ እስከ ሃምሌ 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በክልሉ ከባድ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ 11,749 ነዋሪዎችን አፈናቅሏል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደገለፀው ተፈናቃዮቹ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኑ ሲሆን፣ ደረጃቸውን ባልጠበቁ እና በተጨናነቁ መጠለያዎች ማለትም እንደ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ተቋማት እንዲሁም አደባባይ ላይ ይገኛሉ፡፡ ተፈናቃዮቹ እለታዊ የምግብ ፍጆታቸውን ለመሙላት የእፅዋት ቅጠሎችና ስሮች ላይ ጥገኛ ሆነዋል፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት 72 በመቶ የሚሆነው የሰብል መሬት (በአብዛኛው በቆሎ) የተጎዳ ሲሆን በአማከይ ስምንት በመቶ የቤት እንስሳት በይበልጥ ዶሮች በአደጋው ሞተዋል ተብሏል፡፡ ንብረት እና ማህበራዊ መሰረተ ልማቶችም ወድመዋል፡፡
የመጠጥ ውሃ ማስተላለፊያዎች በጎርፍ ተባላሽተዋል ወይም ተበክለዋል፡፡ ችግሩ በተከሰተባቸው 10 ወረዳዎች ውስጥ ከሚገኙ 917 የውሃ ማስተላለፊያዎች ውስጥ 270ዎቹ ከአገልግሎት ውጭ የሆኑና ጥገና የሚሹ ናቸው፡፡ ከ77 ያላነሱ የጤና ተቋማት በ12ቱ ወረዳዎች በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የተጎዱ ሲሆን በእነዚህ አካባቢዎች ያለውን ህዝብ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዳይሆን አድርጎታል፡፡
ተፈናቃዮች ባሉባቸው ቦታዎች ከመጠን በላይ ባለው መጨናነቅ ምክኒያት በንፁህ የመጠጥ ውሃ እና ንፅህና ጉድለት በውሃ ወለድ በሽተዎች የመያዝ፣ እንዲሁም በእከክ፣ በኩፍኝ እና በመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን በሽታዎች የመያዝ እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የጎርፍ አደጋው ቢያንስ 135 ትምህርት ቤቶችን (99 እነደኛ ደረጃ እና 35 ሁለተኛ ደረጃ) እና 56,006 የሚሆኑ ህፃናት፤ ትምህርታቸው ላይ ተፅዕኖ አድርሷል፡፡
ምን እንኳ የፌዴራሉ መንግሰስት እና የሰብዓዊ እርዳታ አጋሮች የጎርፍ አደጋ ምላሽን ቀስ በቀስ እያሻሻሉ ቢሆንም አሁንም ካለው ፍላጎት ጋር ስለማይጣጣም፤ የተባበሩት የመንግስታት ድርጅት የዝናብ መጠኑ ቀጣይንት ያለው በመሆኑ ተጨማሪ የጎርፍ አደጋው ክፍተኛ መሆኑን አስጠንቅቋል፡፡ አስ