ዜና፡- በሽራሮ ከተማ ቢያንስ 40 ሰዎች ከህግ አግባብ ውጪ በኤርትራ ወታደሮች ተገድለዋል፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል

ትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ የኩናማ ማህበረሰብ አባላት ከባድ ጥቃት ደርሶባቸው ከቀያቸው ተፈናቅለው በቅርቡ በDW ቴሌቪዥን ቀርበዋል።

አዲስ አበባ፣ጥቅምት15/ 2015 ዓ.ም፡- በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን ሽራሮ ከተማ ከጰጉሜ 1 አስከ መስከረም 2 ቀን 2015 ዓ/ም ቀን የኤርትራ ወታደሮች ቢያንስ 40 ሰዎችን ከህግ አግባብ ውጭ መገደላቸውን አምንስቲ ኢንተርናሽናል ትላንት ባወጣው ሪፖርት ገለፀ። ከተጠቂዎች መካከል የኤርትራ ስደተኞችም አንደሚገኙበት ሪፖርቱ አክሎ ገልጧል።

የአምነስቲ ሪፖርት አንደገለፀው በነሐሴና መስከረም ወር ብቻ በመቐለ እና ዓዲ ዻዕሮ በርከት ያሉ የአየር ጥቃት የደረሱ ሲሆን “ ህጻናትን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን  ተገድለዋል”። አምነስቲ አክሎም በትግራይ ክልል አየተባባሰ የመጠው ግጭት አዲስ ግፍ ሊፈጸም ይችላል የሚል ፍራቻ በመኖሩ ተፋላሚ አካላት በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት እንዳያደርሱ አሳስቧል ።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ሙሌያ ምዋናያንዳ  “ከህዳር 2013 አስከ ሰኔ 2014 ዓ/ም   የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና አጋር ኃይሎች አከባቢዎቹን ሲቆጣተሩ የነበሩት፤ ግድያ፣ ጾታዊ ጥቃትና  መጠነ ሰፌ የመብት ጥሰቶች አንደገና ሊከሰት ይችላል”  ሲሉ ስጋታቸው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ ሰራዊቱ የአለምአቀፍ ህግጋትን “በጥብቅ አንደሚያከብር” አንዲሁም በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚደርሰዉን ጉዳት ለመከላከል በከተማዎች ላይ ውጊያ እንደማያደርግ ገልጧል።

የአለም አቀፍ ማህበረሰብ የኤርትራ ኃይል ከኢትዮጵያ ለቆ አንዲወጡ ጥሪ ቢያቀርብም  የኢትዮጵያ መንግስት ግን ዳግም ተቀስቅሶ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የኤርትራ ሃይሎች ስለ መሳተፋቸው ያለው ነገር የለም፡፡ ህዳር 2013 የተጀመረውን ጦርነት በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ውድመት ያደረሰ ሲሆን ጦርነቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ሰላም እንዲሰፍን በርካታ ሙከራዎችን ያሳየበት ቢሆንም  እርቅ ሳይደረግ ቆይቷል፡፡

ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ መጋቢት ወር 2014 ዓ/ም የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል መግባቱን ያመነች ሲሆን ጠቅላይ ሚኒሰትር አብይ ዐህመድ “የኤርትራ ጦር በህዝባችን ላይ ያደረሰው ጉዳት ተቀባይነት የለውም” ሲሉ ለፓርላማ አባላት መግለጻቸው ይታወሳል። 

የኤርትራ ኃይሎች በትግራይ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የፈጸሙት ጥቃት በሰብአዊ መብት ድርጅት የተሰነደ ሲሆን  በኢትዮጵያ መንግስት የሚደገፈው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጭምር በታሪካዊቷ አክሱም ከተማ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣና ጥቃት መፈጸሙን የሰነደው ሪፖርት ያመላክታል።

የአምነስቲ  መግለጫውን ያወጣው የፌደራል መንግስት እና የትግራይ ተወካዮች በአፍሪካ ህብረት መሪነት ለሚካሄደው የሰላም ድርድር በደቡብ አፍሪካ የሰላም ንግግር ያደረጋሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ወቅት ነው፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.