በምህረት ገ/ክርስቶስ @Mercy
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26/2015 ዓ.ም፦ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ሀርቡ ወረዳ በጃራ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣብያ የሚገኙ ተፈናቃዮች በአንድ ሳምንት ውስጥ 256 ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን በሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምርያ የህብረተሰብ ድንገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ባለሞያ አቶ ጀማል አደም አዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።
በፌደራል መንግስትና የትግራይ ሃይሎች መካከል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ከቤት ንበረታቸው ተፈናቅለው በጃራ መጠለያ ጣብያ የሚገኙ ስደተኞች በወባ በሽታ በክፍተኛ ሁኔታ መጠቃታቸውን የገለጹት አቶ ጀማል በተጭመሪም ለሌሎች በሽታዎችየግብረ-ሰናይ ድርጅቶች የድህንነት ስጋት ሰላለባቸው ለሌሎች በሽታዎች በቂ የህክምና መድሃኒትና ቁሳቁሶችን ማቅረብ ባለመቻላቸው የሚፈለገውን የህክምና ግልጋሎት መስጠት አልተቻለም ብለዋል።
“በሽታው በጃራ የስደተኞች መጠልያ ጣብያ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ሰሜን ወሎ ወረዳውች ጭምር የተከሰተ ሲሆን በመጠልያ ጣብያው በቀን ውስጥ ከ 31 እስከ 51 ሰዎች እየተጠቁ ነው፤ አካበቢው ወባ በስፋት የሚራባበት ቦታ በመሆኑ ተጠቂዎች እንዲበራከቱ አድርጎታል” ብለዋል አቶ ጀማል።
አክለውም “በሽታው በየአመቱ ክረምት ላይ ይከሰታል ተብሎ ስለሚጠበቅ አስቀድመን የመከላከል ስራ ስንስራ ቆይተናል በዚህም 10ሺ አንጎበር ለህጻናት፣ ለሚያጠቡ እናቶችና የተለያዩ የኢንፌክሽን በሽታ ላለባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ያሰራጨን ቢሆንም በመጠልያ ጣብያው በበሽታው የሚያዙ ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል” ብለዋል፡፡
በጃራ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ለወባ በሽታ የሚሆን ከወረዳው ጤና ቢሮ ጋር በመነጋገር ለጊዜው የሚሆን የህክምና ቁሳቁስ ቢኖርም ለሌሎች በሽታዎች ማለትም ለአንቲ ባዮቲክ የሚሆን መድሃኒት ግን ከፍተኛ አጥረት እንዳለ አቶ ጀማል አክለው ተናግረዋል።
መጠለያው ውስጥ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የህክምና ባለሙያ፤ በዞኑ እስተዳደር የህክምና እና የባለሞያ ድጋፍ እየተደረገ ሞሆኑን ነው የገለጹት።
የአማራ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መስከረም 23 ቀን የወባ ወረርሽኝን መቆጣጠር እና መከላከል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የምክክር መድረክ ያደረገ ሲሆን በመድረኩ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ ወባ የአማራ ክልልን እያጠቃ ያለ በሽታ እንደሆነ እና በተለይም ምርታማ ቦታዎችና ቆላማ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ የወባ ሥርጭት እንዳለ ገልፀዋል።
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልከሪም መንግሥቱ የወባ በሽታ ስርጭት ከሳምንት ሳምንት እየጨመረ በመሆኑ በልዩ ትኩረት በመሥራት የወባ ወረርሽኝን መቆጣጠር እንደሚገባም ተናግረዋል። እክለውም ለበሽታው ትኩረት በመስጠት ከንግግር ባለፈ ወደ ተግባር መቀየር እንዳለበት ማሳሰባቸው ይታወቃል፡፡አስ