አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 5፣ 2014 ዓም፣ ዛሬ በደሴ ከተማ ፣ ሳላይሽ ቀበሌ ፣ ሰኞ ገበያ አካባቢ ቆራሊዮ ከመኪና ሲያራግፉ በነበሩ ሰዎች ላይ ቦምብ ፈንድቶ ከ11ሰዎች በላይ ሲቆስሉ፣ በእንሰሳት ላይም የሞትና ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የደሴ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።
መረጃውን ከቦታው ያደረሱት የሰኞ ገበያ ሶስተኛ ዋና ጣቢያ ወንጀል መርማሪ የሆኑት ም/ሳጅን ታመነ ምህረቱ እንደሆኑ ቢሮው ጠቅሶ ከቀኑ 5:30 ላይ በሰኞ ገበያ ክፍለ ከተማ ሳላይሽ ቀበሌ አስተዳደር በር ላይ ቆራሊዮ መጋዘን ከመኪና ላይ ወርዶ ሚዛን ሲመዘን ከነበረ ኬሻ ውስጥ በፈነዳ ቦንብ 11 ሰዎች ላይ ጉዳት ሲያደርስ ሶስት በጎችን እና አንድ ፍየልን ገድሎ 15 በጎችን ለጉዳት የዳረገ መሆኑን ምክትል ሳጅን ታመነን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ቢሮው አክሎም በቦታውም የበኣል የፍየል እና የበግ ግብይት ስለነበር ብዙ ሰዎች እና እንስሳት እንዲጎዱ ምክንያት እንደነበር ሃላፊው እንደነገሩት ገልጿል።
በጉዳቱ በግ ሲገዙ የነበሩ ሰዎችና የቀን ሰራተኞች ላይ ጉዳት መድረሱ የተገለጸ ሲሆን ተጎጂዎች ወደ ሆሰፒታል ተወስደዎልም ተብሏል።አስ