አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20/2015 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ የአትክልት እና ፍራፍሬ አመጋገብ ባህል እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ አንድ ጥናት አመላከተ፤ ጎረቤት ሀገራት ከኢትዮጵያ በተሻለ ደረጃ ተጠቃሚዎች መሆናቸውም ተገልጿል። ይህም በቀላሉ ልንከላከላቸው የምንችለው በሽታዎች ተጋላጭ እንዳደረገን ጥናቱ አስታውቋል።
አትክልክት እና ፍራፍሬ እንዳንመገብ እንቅፋት የሆነብን የዋጋው መወደድ እና ያለን ገቢ አነስተኛ መሆኑ እንደሆነም በጥናቱ ተጠቁሟል። ይሁን እንጂ ይላል ጥናቱ፣ ደህና ገቢ ያላቸው ኢትዮጵያውያንም ጭምር የአትክልት እና ፍራፍሬ አጠቃቀም ባህላቸው አናሳ ነው፤ የአለም የጤና ድርጅት በምክረ ሀሳብነት ካቀረበው መመገብ ያለብን የአትክልት እና ፍራፍሬ መጠን ጋር ሲነጻጸር ባለሃብት ኢትዮጵያውያን የሚመገቡት አነስተኛ ነው ተብሏል።
የኢትዮጵያውያንን የአትክልት እና ፍራፍሬ አመጋገብ ባህል ለማሳደግ እና በከተሞች አቅርቦቱ በበቂ ሁኔታ እንዲኖር ለማስቻል ትልቁን ሚና ሊጫወቱ የሚችሉት ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ማለትም ነጋዴዎች እና ቸርቻሪዎች መሆናቸውን ጥናቱን ያካሄደው ተቋም CGIAR በምክረ ሀሳብነት አስቀምጧል። ይህም እንዲሳካ ለነጋዴዎቹ እና ቸርቻሪዎቹ ማነቆ የሆኑ ችግሮችን መፍታት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብሏል።
ዋነኛው ሊቀረፍ የሚገባው ችግር በአቅርቦት እና ሽያጭ ላይ ያለውን ሰንሰለት ማስተካከል እና መደገፍ መሆኑን የጠቆመው ጥናቱ ሁለት ሰንሰለቶችን ማለትም አዲስ አበባን እና ባቱ ከተሞችን በአብነት አስቀምጧል። ወነኛው ችግር የገበያ ዋጋው ተጨባጭ አለመሆን እና ተለዋዋጭ መሆኑ ተገልጿል። ሌላኛው ደግሞ በቂ ማቀዝቀዣ አለመኖሩ ወደ ገበያ የሚቀርበው አትክልት እና ፍራፍሬ የመበላሸት እድሉ ስለሚሰፋ በነጋዴዎች እና በቸርቻሪዎች የሚፈጥረው ስጋት መሆኑን አመላክቷል። አስ