አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16/2015 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ ባለፈው አመት ነሃሴ ወር የተከሰተው የኮሌራ ወረርሺኝ 156 ሰዎችን መግደሉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያወጣው ሪፖርት አመላከተ። ከሚያዚያ 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ 85 በመቶ የሚሆን ተጨማሪ በወረርሽኙ መያዛቸው የተረጋገጠ በሽተኞች መገኘታቸውን ሪፖርቱ አካቷል። በኮሌራ የተያዙ ከ11 ሺ በላይ ሰዎች መኖራቸውን አስታውቋል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ እስካሁን በምስራቅ አፍሪካ ከተከሰቱ ወረርሽኞች ብዙ ግዜን ያስቆጠረ ነው ሲል ተመድ በሪፖርቱ ገልጿል። ቀጣይ ወራቶች ዝና የሚስተናገድባቸው በመሆናቸው ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችል እና ይህም የኮሌራ ወረርሽኝ እንዲስፋፋ የማድረግ እድሉ ሰፊ መሆኑን ጠቁሟል።
በአፍ የሚወሰድ የኮሌራ ክትባት ውስን አቅርቦት መኖር፣ በቂ የውሃ አቅርቦት አለመኖር የአካባቢ ጽዳትና የግል ንፅህና አጠባበቅ እንዳይኖር ማድረጉ ሰባት ነጥብ ሰባት ሚሊየን የሚሆኑ ወረርሽኙ በተከሰተባቸው አከባቢ የሚኖሩ ሰዎችን ለአደጋ እንዲጋለጡ ማድረጉን ተመድ በሪፖርቱ አስታውቋል።
ወረርሽኙን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት ተጨማሪ ፈንድ እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሪፖርቱ አሳስቧል። አስ