ዜና፡ በአዲስ አበባ የአሜሪካ አምባሳደር ትሬሲ እና አዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጀልዴ በአዳማ ከተማ ተወያዩምስል፡ የአሜሪካን ኤምባሲ

በብሩክ አለሙ @Birukalemu21

ሐምሌ 19፣ 2014 ዓም፣ አዲስ አበባ፦የአሜሪካ ኢምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ  አምባሳደር ትሬሲ  አን ጃኮብሰን ትናንት በአዳማ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ተገኝተው ከከተማዋ ከንቲባ ከአቶ ኃይሉ ጀልዴ ጋር ስለ ከተማዋ ልማትና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጀልዴ ከአምባሳደሯ ጋር በስፋት ስለ አዳማ ከተማ ተወያይተናል በተለይም ከተማዋ ያለችበትን የልማት  እንቅስቃሴዎችን  እንዲረዱ አድርገናል አሁን ያለውን የከተማዋን  የልማት ስራዎችንም በተመለከተ ድጋፍ እንዲያደረጉ ጠይቀናል ብለዋል፡፡ አክለውም በዚህም ውይይት አዳማ ከተማ ሰፊ ህዝብ ያላትና ህዝቦቿ  በአንድነተ በመስራት ተቻችሎ የሚኖር ሰላም ወዳድ መሆኑን  እንዲረዱ አድርገናል እነሱም ከእኛ ጋር የሚሰሩትን ነጥቦች አንስተው ተወያይተናል ብለዋል፡፡

ስለ ሀገር ፀጥታ ጉዳም አንስተን ተወያይተናል ያሉት ከንቲባው የከተማዋ ህዝብ ተቻችሎ የመኖርና የመረዳዳት ተሞክሮ ያላው መሆኑንና ይህም ለሃገሪቱ ተምሳሌት ጭምር በመሆኑ እኛም እንደ አመራር የሚጠበቅብንን እየተወጣንና  የህንንም ተግባራችንን አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን  አስረድተናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

አቶ ኃይሉ የወጣቶችን የስራ አጥነት ችግር ለመፍታት እየሰራን ያለነውን  ስራዎችን  በተመለከተም  ማብራሪያ  ስጥተናቸዋል ብለዋል፡፡  አክለውም እየሰራን ያለነው የልማት ስራዎች የስራ አጦችን ቁጥር አየፈታ እንደሚገኝ አስረድተናል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

አምባሳደር ትሬሲ በበኩላቸው ከተማዋ የባህል ብዛህነት ያላትና በቀን ከ 6ሺ በላይ ጎብኚዎችን  የምታስተናግድ እንዲሁም የምክክርና የሰላም ግንባታ ማእከል መሆኗን ጠቅሰው የከተማዋ ነዋሪዎች ስለ ሃገራዊ ጉዳይ ምክክር ሲደረጉ መቆታቸው ከከንቲባው መስማታቸውን በመግለፅ እንዲ አይነቱ ምክክርም ለሃገር ሰለም ጉልህ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡

አምባሳደሯ አክለውም ከተማዋ ስለ ልማት ያላት እቅዶች እና ሁሉንም አሳታፊ ልማቶች እየተከናወኑ መሆኑን ማየታቸውን ገልፀው ሰላምን ለማስፈን ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረግ አለበት ብላዋል፡፡ስለሆነም ከአዳማ፣ ከኦሮሚያ እንዲሁም ባጠቃላይ ከኢትዮጵያ ጋር በሰላም ግንባታና በልማት ላይ ያለንን ግንኙነት አጠናክረን መቀጠል እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

አምባሳደሯ የጤና ዘርፉንም ለማሳደግ እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀው በከተማዋ በ3 ሚሊዮን ዶላር በአሜሪካ መንግስት የተገነባው ላብራቶሪ 20 ሚሊዮን የሚሆኑ የክልሉ ነዋሪዎችን  ተጠቃሚ እንደሚያደርግም አንስተዋል፡፡

የአዳማ ከተማ ከንቲባ ለአምባሳደሯና ለልኡክ ቡድናቸው የኦሮሞ ባህል አልባሳትን በስጦታ መልክ አበርክተውላቸዋል፡፡ አስ 

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.