በምህረት ገ/ክርስቶስ @MercyG_kirstos
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2015 ዓ/ም፡- በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ዙርያ ልዩ ቦታው ጉረ እንዳባጋብር በተባለ ቦታ በኤርትራ ወታደሮች ጥር 10፣ 2015 ዓ.ም. ታፍነው የተወሰዱት 10 ወጣቶች የገቡበት ባለመታወቁ ቤተሰቦቻቸው መጨነቃቸው ገለጹ።
አዲስ ስታንዳርድ እገታውን በተመለከተ ልጆቻቸው ከታገቱባቸው ሶስት ቤተሰቦች ጋር በደረገው ቃለ ምልልስ ቤተሰቦቹ ልጆቹን ለመፈለግ የኤርትራ ወታደሮች ሰፍሮበታል ወደ ተባለበት ወደ ሸረ አካባቢ መጓዛቸውን ገልፀው በቦታው ሲደርሱ ግን ወታደሮቹ የሉም መባላቸው ገልጸዋል።
ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የታጋች ቤተሰብ አንዳሉት ከሆነ ቤተሰቦቹ ወደ ሽረ የተጋዙት ከታፈኑት 10 ወጣቶች መካከል አንዱ በሽረ ዙሪያ እንዳለ የጽሑፍ መልእክት ከተላከላቸው በኋላ ነው ብለዋል።
“ታጋቾቹን ለማግኘት እና ሁኔታቸውን ለማየት ወደ ሽረ ተጉዘን ልናገኛቸው አልቻልንም” ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግሯል።
ሁለት ልጆቻቸው እና አንድ የእህታቸው ልጅ የታገቱባቸው አባት ልጆቻቸው ያሉበትን ቦታ እንደማያውቁ ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግሯል።
“በሽረ ለአራት ቀናት ያህል ቆይተናል፡፡ ሌሎች የቤተሰብ አባላትም ወደ ሽራሮ በመሄድ ያሉበትን ለማወቅ ብንጥርም አልተሳካልንም” ብለዋል፡፡ አክለውም ታጋቾቹ ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውና የታጣቂዎች አባል ያለሆኑ ሰላማዊ ዜጎች እንደሆኑ ገልፀው ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት ደፋ ቀና ሲሉ የነበሩ ንጹሃን ዜጎች ናቸው ብለዋል።
ለድህንነታቸው ሲባል ሰማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉት ከታገቱት ወጣቶች መካከል የአንዷ ወጣት አባት፣ ልጃቸው ስላለችበት አካባቢም ሆነ ሁኔታ ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል።
“ጉዳያችንን ለምስራቅ ዞን የጸጥታ ሀላፊ አሳውቀን ነበር፤ ለሚመለከተው አካል እንደሚያሳውቅና ወደ ቀያችን እንድንመለስ ነግሮን የልጆቻችን ሁኔታ ሳናውቅ ወደ ቤታችን ተመልሰናል” ብለዋል አባትየው፡፡
“ልጆቻችን የት እንዳሉ አናውቅምና ልጆቻችንን ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉልን እንፈልጋለን” ሲሉም አክለዋል።
ሌላኛው የአይን አማኝ እና ከታገቱት የአንዱ የቤተሰብ አባል “ወጣቶቹ ማይ ሸክ በሚባል ወንዝ አካባቢ ወርቅ በማውጣት ላይ እያሉ ነው የታገቱት” ብለዋል።
የእይን እማኞች ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት የኤርትራ ወታደሮች ማይ ሸክ በሚባል አካባቢ በባህላዊ ማዕድን በማውጣትና የውርቅ በማጠብ ስራ ላይ የተሰማሩ ከ40 የማያንሱ ሰዎች ወደሚገኙበት ወንዝ ድረስ በመሄድ ሴቶችና አዛውንቶች ጨምሮ ሁሉንም በአንድ ቦታ ሰብስበው እንደነበሩ ገልጿል። ለሁላቸውም እጃቸውን ወደኋላ አስረው ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ደብድቧቸዋል፡፡ ከዚያም አረጋውያን ሴቶችን ፈትተው 12 ወጣቶችን በአከባቢው ወደ ሰፈሩበት ካምፕ ወሰዷቸው፡፡ ከአንድ ቀን በኋላ ሁለት ታጋቾችን የለቀቋቸው ሲሆን ቀሪዎቹ እድሜያቸው ከ 16 እስከ 24 የሆኑትን ታጋቾች ጥር 12 ቀን ከአክሱም ለቀው ሲወጡ ወዳልታወቀ ቦታ ይዛቸው ሄደዋል።
በአክሱም ከተማ ዙሪያ የሚገኘው የላዕላይ ማይጨው ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት ወ/ሮ አበባ ተስፋይ በአክሱም ከእንዳባጋቢር መንደር ዘጠኝ ወጣቶች ታፍነው በኤርትራ ወታደሮች ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋግጠዋል።
“የኤርትራ ወታደሮች በወጣቶች ላይ የሚፈፀመውን አፈና እናውቃለን፣ ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የክልል የመንግስት አካላትም አሳውቀናል” ብለዋል ወ/ሮ አበባ።
የኤርትራ ወታደሮች ከቦታው ለቀው ከወጡ በኋላ ወደ አስተዳደራቸው የተመለሱት ወ/ሮ አበባ አፈናው የተካሄደው መንደሩ በኤርትራ ቁጥጥር ሰር በነበረበት ከጥቂት ሳምንታት በፊት መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ያረጋገጡ ሲሆን ይህም በቦታው በድብቅ የነበሩ የአከባቢው አስተዳደር አባላት አረጋግጠውልናል ብለዋል።
በትግራይ በተደረገው የሁለት አመታት ጦርነት የኤርትራ ወታደሮች ከፌደራል ሃይልና ከአማራ ክልል ታጣቂዎች ጋር በመተባበር ጦርነት ዉስጥ የተሳተፉ ሲሆን በጦርነቱም ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰትና የጀምላ ጭፍጨፋ መፈጠማቸውን የተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች በሪፖርታቸው ጠቅሰዋል፡፡
በህዳር 2013 ዓ/ም መጨረሻ ላይ በአክሱም ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች እንዲሁም የ13 አመት ታዳጊዎች ሳይቀር የጭፍጨፋው አካላት ሆነዋል፡፡ ይህንን ጭፍጨፋም በዋናነት የተፈጸመው የኤርትራ ወታደሮች መሆኑን ተጨባጭ ማስረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወንጀለኞችን አጣርቶ ተጠያቂ እንደሚያደርግ ቃል ገብቶ እንደነበር የሚዘነጋ ጉዳይ አይደለም፡፡ የኤርትራ ሃይሎች የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶችን እና ህጻናትን ሰላማዊ ዜጎችን ጨምሮ በመግደላቸው፣ ንብረት በማውደምና በመዝረፍ ተከሰዋል።
የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ለቀው እንዲወጡ በፌዴራል መንግስትና በትግራይ ባለስልጣናት መካከል የተደረገው የሰላም ስምምነት ቢደነግግም በቅርቡ የትግራይ ክልል መሪ ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) አማካሪና አቶ ጌታቸው ረዳ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ የኤርትራ ሃይሎች በብዛት ቢወጡም የትግራይ ባለስልጣናት ወታደሮቹ አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች እንደሚቀሳቀሱ ያውቃሉ ብሏል። በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና በትግራይ ባለስልጣናት መካከል የተደረገውን ስብሰባ አስመልክቶ አቶ ጌታቸው “ይህንን በውይይታችን አንስተናል” ብለዋል። የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ እንዲወጡ በፌደራል መንግስት ተጠይቀዋል ያሉ ሲሆን አክሎም ከትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች መውጣታቸው በአፍሪካ ህብረት ክትትል ቡድን መረጋገጡን ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የኤርትራ ጦር እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ገልጿል። እነዚህ አካባቢዎች በትግራይ ሰሜን ምእራብ ክፍል የሚገኘው አዲያቦ እና ኢሮብ በሰሜን ምስራቅ የትግራይ ክፍል የሚገኙ ሲሆን አቶ ጌታቸው “በጣም አሳሳቢ” ሁኔታ እየፈጠረ ነው ብለዋል። የፌደራል መከላከያ ሰራዊት ድንበሩን ለመጠበቅ በእነዚህ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ እንዲሰማራ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል።
የኤርትራ ጦር በትግራይ ክልል እስካሁን መኖሩን ከሚገልፁ ዘገባዎች በተቃራኒ አንድ የኢትዮጵያ ጦር ጄኔራል በትግራይ ክልል ከፌዴራል ጦር በቀር ሌላ የጸጥታ ሃይል የለም ሲሉ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ሰሜናዊ ትግራይ ክልል ለሁለት አመታት የተካሄደውን ጦርነት እንዲሁም በሰላም ስምምነት የቋጨችውን ጦርነት አስመልክቶ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በእሁድ በሰጡት ቃል “የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ አላወጡም፣ ወታደሮቿ ሰዎችን ገድለዋል…የሚሉ ውንጀላዎች የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ እንዳይሆን ያደርጋል ሲሉ አጣጥለዋል።አስ