በአሰፋ ሞላ
አዲስ አበባ፣መስከረም 23/2015 ዓ.ም፡- የአማራ ክልል ከሐምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 2015 ዓ.ም አጋማሽ ድረስ ከ163 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ መያዛቸውን ተዘገበ።
መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ከባለድርሻ አካላት ጋር ከመስከረም 15 በኋላ የሚከስተውን የወባ ወረርሽኝ ለመከላከል የውይይት መድረክ ያከሄደ ሲሆን በመድረኩም ባለፈው ሳምንት ብቻ 3 ሺህ በወባ የተያዙ ሰዎች ሪፖርት መደረጉ ተገልጧል፡፡
የኢንስቲቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ የወባ ወረርሽኝ ተጋላጭ በሆኑ ወረዳዎች እና ዞኖች በልዩ ሁኔታ የመከላከል ስራ ካልሰራን ችግሩ ከፍ ያለ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል ብለዋል። ዳይሬክተሩ አያይዘዉም በጤና ኬላዎች የወባ ህክምና በተገቢው መንገድ እንዲሰጥ ሊደረግ ይገባልም ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ በበኩላቸው፣ የወባ በሽታ ስርጭት ከፍ ማለቱን ያነሱ ሲሆን፣ ለዚህም የጤና ባለሙያዎችጋር በትኩረት ከሰራን በወባ ምክንያት ሞት እንዳይከሰት ማድረግ እንችላለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ላይ በክልሉ የሚገኙ የሁሉም ዞኖች የጤና መምሪያ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። አስ