ዜና፡ በቢሾፍቱ የአራት ፖሊሶችን ህይወት ያጠፉት ታጣቂዎች ድርጊቱን የፈፀሙት የጦር መሳሪያ ለመዝረፍና እስረኞችን ለማስለቀቅ ነው ሲል የከተማው ኮሙኒኬሽን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8/2015 ዓ.ም፡- በቡሾፍቱ ከተማ ጨለለቃ ክፍለ ከተማ ጌትሽ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ አራት የፖሊሶ አባላት ህይወት አልፏል፡፡ የከተማው ኮሙኒኬሽን ሃላፊ ደጀኔ በጂሮ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለፁት “ታጣቂዎቹ ድርጊቱን የፈፀሙት የጦር መሳሪያ ለመዝረፍና በህግ ጥላ ስር የሚገኙ እስረኞችን ለማስለቀቅ ነው: ነገር ግን ሊሳካላቸው አልቻለም” ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ ኮሙኒኬሽን ሃላፊ ደጀኔ በጂሮ “እሁድ እለት ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ሲሆን ማንነታቸው ያልታወቁ ሃይሎች በጨለለቃ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ላይ ተኩስ ከፍተው በጥበቃ ላይ የነበሩ አራት የፖሊስ አባላትን ገድለዋል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለተወሰኑ ደቂቃዎች የተኩስ ልውውጥ ያደረገው ይህ የታጠቀ አካል ዘራፊ ወይም ሽፍታ ሳይሆን እንዳልቀረ ጠቅሰው ፖሊስ ምንነታቸውን ለማጣራት ምርመራ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡ ይህ ታጣቂ ቡድን ሰላማዊ ሰው በመምሰል እየተንቀሳቀሰ ባለበት ቅፅበት ነው ፖሊስ ጣቢያው ጠባቂዎች ላይ ተኩስ የከፈተው ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ አስረድተዋል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.