ዜና፡ በሸዋ ሮቢት ከተማ የገቢዎች ጽ/ቤት ሰራተኛ ግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ

ወ/ሪት ጽዮን ተገኝ: ፎቶ-የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14/2015 ዓ.ም፡- በሸዋ ሮቢት ከተማ 06 ቀበሌ ቆቦ ልዪ ስሙ አጤሳ በተባለ አካባቢ ህዳር 14/ 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ስዓት በተተኮሰ ሁለት ጥይት በተገደለችው ወ/ሪት ጽዮን ተገኝ ወንጀል የተጠረጠረው ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

ምርመራውንም በተገቢው መንገድ በማድረግ ተገቢውን ቅጣት እንዲቅጣና ፍትህ እንዲረጋገጥ ይደረጋል ሲል ጽ/ቤቱ አያይዞ ገልጿል፡፡

የህዝብ አገልግሎት በሚሰጥባቸው መዝናኛ ቦታዎች እና በየመንገዱ መሳሪያ ይዞ በመገኘት በየአካባቢው አላግባብ በሚተኮሱ ወንጀሎችን ለመቀነስ ከተማ አስተዳደሩ እገዳዎችን በማውጣት ቅድመ ወንጀል መከላከል ስራዎችን መስራቱንም ጽ/ቤቱ ገልጿል።

ሆኖም ግን አንዳንድ ግለሰቦች በግዴለሽነትና በስርአት አልበኝነት የተጣለውን ክልከላ በመጣስ በወንጀል ድርጊት ውስጥ እየተሳተፉ በመሆናቸው፣ ህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ወንጀልን በጋራ እንዲከላከል የከንቲባ ጽ/ቤቱ በፌስቡክ ገጹ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት ሰራተኛ የሆነችው ወ/ሪት ጽዮን ተገኝ ህዳር 13  ምሽት 12 ስአት አካባቢ ቤተሰብ ለመጠየቅ በባጃጅ ላይ እያለች ነበር አቅጣጫው ካልታወቀ ቦታ በተተኮሰ ጥይት ህይወቷ ሊያልፍ የቻለው፡፡

በተመሳሳይ መልኩ የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም  ከምሽቱ 3 ስዓት ገደማ  ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት መገደላቸው ይታወሳል፡፡ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት “የተሰጣቸውን የህዝብ አደራ ለመወጣት ውሎአቸውን በስራ ተጠምደው ለእረፍት” ወደ ቤታቸው ከመኪና ላይ ወርደው ሊገቡ ሲሉ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰባቸው ጥይት መገደለቸውን የከተው አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት  አስታውቆ ነበር።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.