ዜና፡ በሸዋሮቢት እና አካባቢው በታጣቂዎችና በመከላከያ ሀይሎች መካከል በተነሳ ግጭት ስድስት ሰዎች ተገድለዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22/2015 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በሸዋሮቢት ከተማ እና አካባቢው፣ ከረቡ  ጀምሮ፣ የተኩስ ድምፅ እየተሰማ እንዳለና ቢበዛ ስድስት ሰዎች እንደተገደሉ የከተማዋን ነዋሪዎች ዋቢ አድርጎ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ዘግቧል

በሸዋሮቢት እና አካባቢዋ፣ “ፋኖ” በተባለው የአማራ ክልል የታጠቁ ወጣቶች አደረጃጀት እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል ግጭት እንደነበር ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

በከተማዋ ከባድ የጦር መሳሪያ ድምፅ ሲሰማ እንደነበር የሚገልፁት የከተማው ነዋሪዎች  መንቀሳቀስ እንኳ አስቸጋሪ ሆኗል ብለዋል፡፡ አንድ አስታየት ሰጪ ትላንት ጠዋት ወደ ስራ የሚሄድ አንድ ሰው መገደሉን ለሚዲያው ተናግሯል፡፡ ሌላ ነዋሪ መንገድ ላይ ሶስት ሰዎች ተገድለው አይቻለው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በግጭቱ ሳቢያ፣ መደበኛ መንግሥታዊ ሥራዎች እስከ መቋረጥ እየደረሱ ነው፤ ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ የደኅንነት ስጋት እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

የ24 ዓመት ታዳጊ ጥቃት ደርሶበት ወደ ሆስፒታል ሪፈር ተፅፎለታል ሲል የገለፀው አንድ አስታየት ሰጪ በከተማ መሃል ከባድ መሳሪያ መቶከስ ህፃናት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ቀላል እንዳይደለ ገለልፀው በተለይ ሸዋሮቢት ላይ ያለው ሁኔታ ከባድ በመሆኑ መፍትሄ ይበጅለት በማለት ጠይቀዋል፡፡

በከተማዋ በርካታ ግድያዎች መፈፀማቸው የሚታወቀ ሲሆን ባሳለፍወነው ሰኔ ወር በሸዋሮቢት ከተማ ሁለት የተለያዩ የመንግስት የፀጥታ ዘርፍ የስራ ሃላፊዎች መገደላቸው አይዘነጋም፡፡ ማክሰኞ ሰኔ 27 የከተማ አስተዳደሩ ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች ተገድለዋል፡፡ በተጨማሪም ምክትል ሳጅን ያለለት ደጉ ሰኔ 29 ቀን ማታ በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር 08 ቀበሌ ከምሽቱ 4 ስዓት በስራ ላይ እያሉ ባልታወቁ ግለሰቦች በጥይት ተደግለዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ሓምሌ 8 ቀን አብዱልከሪም አባጀበል የተባለ ወጣት ማንነታቸው ባልታወቀ ሀይሎች በጥይት መገደሉን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል

ከዚህ ቀደም የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የስራ ባልደረባ የሆነችው ወ/ሪት ጽዮን ተገኝ እና የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው በተለያያ ጊዜ ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸው አይዘነጋም፡፡

የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽ/ቤት የስራ ባልደረባ የሆነችው ወ/ሪት ጽዮን ተገኝ አቅጣጫው ካልታወቀ ቦታ በተተኮሰ ጥይት ሕይወቷ ያለፈው ህዳር 13/ 2015 ዓ.ም  ሲሆን  ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ደግሞ ነሐሴ 26/ 2014 ማታ ከምሽቱ 3 ስዓት ገደማ አካባቢ ነበር ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት የተገደሉት፡፡

የአሁኑን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ የአቶ አብዱ ሁሴን ግድያን ተከትሎ የከተማ አስታዳደሩ ኮማንድ ፖስት፣ ከሰኔ 28/2015 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ክልከላዎችን አውጇል፡፡ ኮማንድ ፓስቱ በከተማዋና በአካባቢዉ የሰላምና የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ እንዲሆን እና ዜጎች ያለ ስጋት ወጥተው የሚገቡበት ለማድረግ ብዙ ጥረት የተደረገ ቢሆንም አሁንም ከተማዋን ሰው አልባ እንድትሆንና ከፍተኛ የጸጥታ ችግር እንዲከሰት ጥረቶች እየተደረጉ በመሆኑ ገልፆ ነበር፡፡

በክልከላውም በከተማዋ ላልተወሰነ ጊዜ ከምሽቱ 12 ስዓት ጀምሮ ማንኛውም ተሽከርካሪ ይሁን የሰው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ተገድቦ በትግበራ ላይ መሆኑ ይታወቃል። በተጨማሪም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የምሽት ክለቦችን ጨምሮ ከምሽቱ 12 ስዓት በኃላ ምንም አይነት አገልግሎት አንዳይሰጡ ክልከላ አድርጓል።

የከተማ አስተዳደሩ የአካባቢው ሰላምና ፀጥታ እንዲረጋገጥ የተለያዩ ክልከላዎችን ቢያስቀምጥም በከተማዋና አካባቢዋ ግጭቶችና ግድያዎች የቀጠሉ በመኆኑ ነዋሪዎች በስጋት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.