ዜና፡ በሲዳማ ክልል ‘ኦነግ ሸኔ’ እና ህወሓትን በገንዘብ በመደገፍ የተጠረጠሩ ሁለት የመንግስት ሰራተኞች እና አንድ የትምህርት ቤት ሥራ አስኪያጅ ፍርድ ቤት ቀረቡ

አቶ ካንባታ ካዊ አቶ ተስፋፅዮን ለገሠ አቶ ምትኩ በላይነህ ። ፎቶ ሶሻል ሚዲያ

በምህረት ገ/ክርስቶስ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 05/2015 ዓ/ም፦ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ሽብርተኛ ተብለው ለተፈረጁት መንግስት “ኦነግ ሸኔ” ብሎ ለሚጠራው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እና ህወሓት የገንዘብ ድጋፍ ታደርጋላቹ ተብላዉ በሲዳማ ክልል ፖሊስ የተጠረጠሩ ግለሰቦች የሰባት ቀን ቀጠሮ ተሰጣቸው።

1ኛው ተጠርጣሪ አቶ ካንባታ ካዊ የደቡብ ክልል ሳይንስና ተክኖሎጂ ኤጀንሲ ሠራተኛ፤ 2ኛው ተጠርጣሪ አቶ ተስፋፅዮን ለገሠ የደቡብ ክልል ግንባታ ዲዛይን ቁጥጥር ባለሥልጣን ሠራተኛ ሲሆኑ 3ኛ ተጠርጣሪ አቶ ምትኩ በላይነህ የታቦር መካነየሱስ ትምህርት ቤት ሥራ አስኪያጅ ናቸው።

ግለሰቦቹ ባለፈው ሃሙስ ጥቅምት 02, 2015 በሀዋሳ ከተማና አከባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ የቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ከጠየቀው ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ዉስጥ 7 ቀን በመፍቀድ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል::

የመጀመርያ የፍርድ ቤት ውሏቸው መስከረም 20 ቀን 2015ዓ/ም አንደነበር አዲስ ስታንዳርድ ከቤተሰብ እንዲሁም ጉዳዩን በቅርበት ከሚከታተሉ ነገር ግን ማንነታቸዉ አንዳይገልጽ ከጠየቁ የቅርብ ሰዉ አረጋግጣለች።

በመጀመርያ የፍርድ ችሎታቸው መርማሪ ፖሊስ ሶስቱንም ግለሰቦች በአንድ የክስ መዝገብ ያቀረባቸው ሲሆን “ለኦነግ ሸኔ እና ህወሓት ሽብር ቡድኖች የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉ” እንደጠረጠራቸው፤ በስማቸውም 30 የባንክ ደብተር አንዳላቸው ፖሊስ ለችሎቱ አስረድቶ ለተጨማሪ ምርመራ የ14 ቀን ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቇዋል።

አንደኛና ሁለተኛ ተጠርጣሪዎች ሲቪል በለበሱና የፍርድቤት መጥርያ ባልያዙ የድህንነት አካላት ተይዘዉ ከፍርድቤት ትአዛዝ ውጭ ለስድስት ቀናት በህገወጥ መንገድ ልዩ ቦታው ጨንጌ በሚባል የክልሉ ልዩ ሃይል ማሰልጠኛ ታስረዉ እንደነበር ሲያስረዱ ሶስተኛ ተከሳሽ ለሁለት ቀናት በማስልጠኛው ታስረዉ እንደነበር ልፍርድቤቱ ማስረዳታቸዉን የአዲስ ስታንዳርድ ምንጮች ጠቁመዋል።

በተጨማሪም መርማሪ ፖሊስ አሸባሪ ቡድን ብሎ ከጠቀሳቸው አካላት ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ጠቅሰዉ በስማቸው 30 የባንክ ደብተር አንዳላቸው የተነገረዉም ከእውነት የራቀና ሆን ተብሎ የተቀናባበረ መሆኑን ገልጸዉ የዋስትና መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ችሎቱን ጠይቀዋል።

ግራና ቀኙን ያየው ችሎቱ ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጭ ፖሊስ ግለሰቦቹን ለስድስት ቀናት በህገወጥ መንገድ ማሰሩን ህጋዊ እንዳልሆነ ጠቅሶ፤ ከህግ ውጭ ለስድስት ቀናት መታሰራቸውን ታሳቢ በማድረግ የ10 ቀን ቀጠሮ (መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ/ም) ስጥተዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በተሰጣቸው የቀን ቀጠሮ መቅረብ የነበራባቸው ቢሆንም የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ድልድይ መደርመስ ጋር ተያይዞ የተፈጠረው አለመረጋጋት ተከትሎ ችሎቱ ለሁለት ቀናት ተራዝሞ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ/ም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተደርግዋል።

ፖሊሰ በተሰጠው የምርመራ ጊዜያት ያጠናቀረውን የተጠርጣሪዎች የወንጀል ምርመራ ውጤት እንዲያቀርብ የተጠየቀ ሲሆን መርማሪ ፖሊስ ማስረጃ ሰብስቦ አለመጨረሱንና ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ጠይቋዋል።

ይህንን የተረዳው ችሎቱም ሰባት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እስከ ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ/ም ፈቅዶ ተከሳሾቹ ማረሚያ እንዲቆዩ ውሳኔ አስተላልፏል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.