ዜና፡- በምዕራብ ኦሮሚያ በአሮሞና በአማራ ዜጎች ላይ ከተፈፀመው ግድያ ጀርባ እራሱን “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጦር አዛዥ” ብሎ የሚጠራው ፈቀደ መኖሩን ዋሺንግተን ፖስት አጋለጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14/ 2015 ዓ.ም፡- በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በአሮሞና በአማራ ዜጎች ላይ ከተፈፀመው ግድያዎች ጀርባ እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጦር አዛዥ ብሎ የሚጠራው ፈቀደ አብዲሳ እና ሃይሎቹ መኖራቸውን ዋሺንግተን ፖስት በዘገባው አመላከተ፡፡ ዘገባው ፈቀደ አብዲሳ እና ሃይሎቹ በክልሉ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን በተደጋጋሚ በጅምላ ሲገድሉ እንደነበር ነዋሪዎች መግለፃቸውን አስታውቋል፡፡

ባሳለፍነው አመት የኦሮሞና የአማራ ብሄር ሰዎችን አሰባጥራ በምታኖረው አጋምሳ ከተማ በኦሮሞ አማፂያን የሚደገፈው የፈቀደ ታጣቂዎች በደርዘን የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆችን ምግደላቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል ብሏል፡፡

“እነዚህ የሞቱት ንፁሀን አማራ ጎረቤቶቻችን ነበሩ” ሲል የተናገረው አንድ የኦሮሞ ነዋሪ ” ለተፈጠረው ነገር ተጠያቂው ፈቀደ ነው” ሲል ኮንኗል፡፡ የፈቀደ ሃይሎች ስፍራው ከሸሹ በኋላ የአማራ ሚሊሻዎች ባደረጉት ጥቃት ከ100 በላይ ኦሮሞዎችን መገደላቸውን  የአይን እማኞች ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል ለረጅም አመታት እየተካሄደ ያለው አመፅ በትግራይ ጦርነት ተሸፍኗል ያለው የዋሺንግተን ፖስት ዘገባ ነገር ግን አመፁ በክልሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ህይወት መቅጠፉን፣ የብሄር ተኮር ሚሊሻ እንዲሰፋፋና ለአገሪቱ መረጋጋት የረዥም ጊዜ ስጋት ፈጥሯል ብሏል።

የታጣቂዎቹ አዛዥ ፈቀደ አብዲሳ በስልክ ከሚዲያው ጋር ባደረገው ቃለ-መጠይቅ በፌዴራል መንግስት እና በአማራ ሚሊሻ እየተፈፀመ ያልውን መድሎ ወይም ጭቆናን እየተዋጋን ያለው ለኦሮሞ ህዝብ መብት ነው በማለት ገልጧል፡፡

ፈቀደ ”ዘራፊና አጋች ነው” እንዲሁም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን በመምሰል ከመንግስታ ጋር ይሰራል የሚለውን ውንጀላ ውድቅ በማድረግ ባሳለፍነው አመት በአጋምሳ በተካሄደው ጥቃት ታጣቂዎቹ ምንም አይነት ሰላማዊ ሰው እንዳልገደሉ ገልጧል፡፡ ፈቀደ ይህን ይበል እንጂ ከሁለቱም ብሄረሮች ማለትም ከኦሮሞ እና አማራ የተውጣጡ 12 ምስክሮች የሰጡት ቃል ከዚህ ጋር ይቃረናል።

“ከህዝባችን ጎን ቆመን እየተዋጋን ነው” በማለት ለዜና አውታሩ የተናገረው  ፈቀደ “ንጹሃን ዜጎችን አናጠቃም…. ይህ ፍጹም ውሸት ነው” ሲል ገልጧል።

ስድስት የወለጋ ነዋሪዎች እንደሚሉት የፈቀደ ታጣቂዎች ገንዘብና ከብቶች እንደሚዘርፉ እንድሁም ሰዎችን በማገት ገንዘብ እንደሚጠይቁ ገልጸዋል፡፡ ነዋሪዎቹ ታጠቂ ሀይሎቹ አንድንድ ጊዜ ከመንግስት የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመተባበር በጃል መሮ ከሚመራው ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር እንደሚዋጉም ተናግረዋል፡፡

ፈቀደ በበኩሉ “በጉልበት የወሰድነው ምንም ነገር የለም” በማለት በፅኑ አስተባብሏል፡፡ ለዜና ምንጩ፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የጦር አዛዥ መሆኑን እና ለጃል መሮ እንደማይታዘዝ ፈቀደ ተናግሯል፡፡ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ግን ፈቀደ እራሱን የታጣቂ ሀይሉ አዛዥ አድርጎ ቢናገርም ከመንግስት ጋር እንደሚተባበር አስታውቋል።

ነሀሴ 12 የኦሮሚያ ክልል መንግስት ሃይሎች አጋምሳ ከተማን ለቀው ከወጡ ከሰዓታት በኋላ ፈቀደ እና ታጣቂዎቹ በከተማዋ ውስጥ መታየታቸውን የገለፁት አራት የኦሮሞ አይን እማኞች ከአራት እስከ 18 የአማራ ተወላጆች በፈቀደ ታጣቂዎች ሲገደሉ ማየታቸውን ተናግረዋል ሲል ወሺንግተን ፖስት በዘገባው አካቷል፡፡ አምስት የአማራ ነዋሪዎች ደግሞ ሟቾቹ 50 እንደሚደርሱ ተናግረዋል፡፡

የጥታቱ ሰለባ ከሆኑት መካከል አንድ ወንድ እና ሴት መኖክሴ ይገኙበታል፡፡ አንድ የአማራ ታዳጊ አባቷን በጥይት መተው መግደላቸውን ገልፃለች፡፡

“ይህ የብሄርን መሰረት ያደረገ ግድያ ለመጀመር የተደረገ ሙከራ ነው” ሲል ከስተቱን አንድ የኦሮሞ ነዋሪ ገልፆታል፡፡

የታጣቂዎች መሪ የሆነው ፈቀደ የእሱ ታጣቂዎች ንፁሃንን ገድለዋል የሚለውን ወቀሳ ውድቅ በማድረግ የሞቱት ሁሉም የአማራ ታጣቂዎች ናቸው ብሏል፡፡ የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች አብረው እንዲኖሩ የሚያበረታታ ንግግር ማድረጉንም ተናግሯል። የአማራ ነዋሪዎችን ደህንነቱ ወደ ተጠበቀ ቦታ መምራቱን ተናግሯል፤ ይህም በሁለቱም ወገኖች ተረጋግጧል ብሏል።

በመቀጠል የፈቀደ ሃይሎች የኦሮሞ ወንዶች በአካባቢው በሚገኝ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሰበሰቡ በማዘዝ የጦር መሳሪያቸውን እንደወሰዱ ስድስት እማኞች ተናግረዋል፡፡ ፈቃደ ይቃወሙኛል ብሎ ያሰባቸውን ኦሮሞዎች ትጥቅ ማስፈታቱን ማረጋገጡን ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡

የኦሮሞ ነዋሪዎች የአማራ ሃይሎች ሲገቡ የፈቀደ ሃይሎች መሸሻቸውን እና የአማራ ታጣቂዎች ህጻናትና አዛውንቶችን ጨምሮ ከ100 በላይ ሰላማዊ ሰዎች መግደላቸውን ተናግረዋል።

ቃላቸውን የሰጡ የአይን እማኞች በአማራ ታጣቂዎች የአጸፋ እርምጃ እንዲወስዱ ባደረገው ጃርተጌ ጃርቴ እና ክሪሙ ከተሞች አቅራቢያ የተፈፀሙ ግድያዎች ላይ ፈቀደ እና የእሱ ታጣቂዎች መሳተፋቸውን ገልፀዋል፡፡ ፈቃደ በዚህ ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ እንዳልነበራቸው ተናግሯል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ የአማራ ዜጎች በኦሮሚያ ክልል ያለውን ግጭት በመሽሽ መሰደዳቸውንና ቁጥራቸው ያልታወቀ ኦሮሞዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን መግለፁን ዘገባው አካቷል፡፡ አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.