ዜና፡ ሶስት የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት በምዕራብ ትግራይ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት እየፈፀሙ ባሉ ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ሓምሌ 18 /2015 ዓ.ም፡- ሶስት የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት በምዕራብ ትግራይ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየፈፀሙ ባሉ ግለሰቦች ላይ አሜሪካ ማዕቀብ እንድትጥልባቸው ጠየቁ፡፡

ብራድ ሼርማን፣ ጀምስ ፒ. ማክጎቨርን እና ሎሊ ዶጌት የተባሉ ሶስት የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ሓምሌ 13  ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ዋና ፀኃፊ አንቶኒ ብሊንከንና ለጃኔት የሌን በፃፉት ደብዳቤ፣ በፌዴራል መንግስትና በህወሓት መካከል ከተደረሰው ዘላቂ ጦርነት የማቆም ስምምነት በኋላ በምዕራት ትግራይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈፀሙ ያሉ ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ጠየቁ፡፡

የኮንግረስ አባሎቹ ብሊንከን “ጥቃት አድራሾችና በኣዛዥነት ደረጃ ላይ ያሉ አካላት ላይ ተጠያቂነት መረጋገጥ አለበት” ሲሉ በወረሃ መጋቢት የሰጡትን መግለጫ በመጥቀስ የአሜሪካ መንግስት በተለይም በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እና በላይ አያለው ላይ የቪዛ እገዳና የፋይናንስ ንብረት ቁጥጥር ማዕቀብ እንዲጥል ጠይቀዋል፡፡

እኝህ ሁለቱ ግለሰቦች እየተካሄደ ባለው በዘፈቀደ እስር፣ ቶርቸር በማድረግና ፣ ስምምነቱን ተከትሎ በተፈፀመው የምዕራብ ትግራይ የዘር ማፅዳት ተግባር ላይ፣ ዋና ተሳታፊ መሆናቸው በሂዩማን ራይስ ወች ተለይቷል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

አባላቱ በደብዳቤያቸው ህዳር 2022 የተደረሰው ቀላቂ የተኩስ ማቆም ስምምነት ሂደትን እንደሚያበረታቱ ጠቅሰው ነገር ግን ከስምምነቱ በኋላ በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተፈፅመዋል ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል ኃይሎችና የፋኖ ታጣቂዎች በምዕራት ትግራይ የዘር ማፅዳት ተግባር እያከናወኑ በመሆኑ የአሜሪካ መንግስት ተጠያቂነት እንዲያረጋግጥና ማዕቀብ እንዲጣሉባቸው እንዲሁም ዘላቂ ሰላምን ለማስፈንን ተጠያቂነት መረጋገጥ ይኖርበታል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የአማራ ሃይሎች፣ እስር እና በትግራይ ንፁሃን ላይ የሚያከናውኑት የዘር ማፅዳት ተግባር መቀጠሉን የገለፁት ሶስቱ አባላት ተጠርጣሪዎቹ ተጠያቂ ለማድረግ የአሜሪካ  መንግስት እርምጃ የሚወስድበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል፡፡

ሰኔ 1 2023 የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ወች የአማራ ታጣቂዎች የትግራይ ንፁሃን ላይ የዘር ማፅዳት ተግባር መቀጠላቸውን በሪፖርቱ ይፋ ማድርጉንና ይህንንም ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአማራ ሀይሎች 10 ሺህ የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆችን ማፈናቀላቸውን ማሳወጡቁን ደብዳቤው ጠቅሶ ከስምምነቱ በኋላ የአማራ ኃይሎችና የፋኖ ታጣቂዎች በትግራይ ላይ የዘር ማፅዳት ዘመቻን ቀጥለውበታል ሲል ከሷል፡፡

ይሀንንም  የተቀናጀ የዘር ማፅዳት ተግባርን ለመከናወን የክልሉ ሃይሎችና የፋኖ ታጣቂ ሃይሎች የትግራይ ንፁሃንን በማሰርና  ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ በማቆየት እንዲሁም በግዳጅ በጅምላ ከቤታቸው ምዕራብ ትግራይ እንዲነሱ አድርገዋል ብለዋል፡፡አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.