ዜና፡ ስለ ጎረቤት አገር ሶማሊያ በ”Etv World” የተላለፈው ፕሮግራም የኢትዮጵያን መንግስት ፖሊሲ የማይወክል መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳወቀ

አዲስ አበባ፣ ጷጉሜ 3/2014ዓ.ም:- የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “Etv World” ማክሰኞ መስከረም 6 ቀን 2014 ዓ.ም. ስለ ሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ሪፐብሊክ ያስተላለፈው ፕሮግራም ትክክለኛ ያልሆነ ዘገባ መሆኑን ገልፆ “የፕሮግራሙ ይዘት የኢትዮጵያን መንግስት ፖሊሲ የማይወክል እና ከሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ጋር የማይጣጣም” መሆኑን አስታወቀ፡፡

በመንግስት ባለቤትነት የሚተዳደው “Etv World” በሰራው ዘገባ “ሶማሊያ በአፍሪካ እጅግ ጥንታዊ የሆነ የእርስ በርስ ጦርነት ስታስተናግድ ቆይታለች። ከአስርት አመታት ቀውስ በኋላ ሶማሊያ አሁንም ያልተረጋጋች እና የበርካታ የታጠቁ ተዋናዮች መኖሪያ ነች ሲል” ያትታል። አክሎም የሚሊዮን ዶላር ጥያቄ ታዲያ የአገር ውስጥ ጌቶች ለሰላም ግንባታ ያላቸው ሚና የት ነው? የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ የሶማሊያን የታሪክ አካሄድ ሊለውጡ ይችላሉ? ሼክ ማህሙድ ሶማሊያን ከአመታት ግጭት አውጥታ ወደ ሰላም መስክ ሊወስዱት ይችላሉ? ከፊት ለፊቱ ምን ፈተናዎች እና እድሎች አሉ? ሲል ይጠይቃል፡፡

ሕወሓት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በሚቃረን መልኩ የፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድን አስተዳደር ለመጥለፍ እንደሚሰራም ዘገባው አመልክቷል፡፡ አክሎም ኢትዮጵያ የሼክ መሀሙድ አስተዳደር የህወሃትን ሙከራ በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ እንደማይቀበል ታምናለች ያለው ዘገባው ነገር ግን ፕሬዝዳንት ሀሰን አስተዳደር ይህን ማድረግ ካልቻለ ለሶማሊያ አደጋ መሆኑንና ለሽብር ቡድኖች ማእከል እንድትሆን ያደርጋታል ሲል ይተነትናል፡፡

ቢሆንም ይህንን ፕሮግራም በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትላንት ምሽት ባወጣው መግለጫ “Etv World”” ስለ ሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ በሚመለከት አየር ላይ ያዋለው ፕሮግራም ትክክለኛ አለመሆኑንና ከሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ጋር የማይጣጣም ነው ሲል ገልጿል።አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.