ዜና፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተማሪዎች መመዝገቢያ ክፍያ እንዲቆም አሳሰበ

በአማራ ክልል የ2015 የትምህርት ዘመን የነበርና አዲስ ተመዛጋቢ ተማሪዎች ከነሃሴ 23 አስከ ጳጉሜ 4/2014 ዓ.ም ይካሄዳል ። ፎቶ፡ የአማራ ብሔራዊ ክለላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 3፣ 2014 ዓ.ም ፦ የአማራ ብሔራዊ ክለላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ትላንት ረቡዕ ጳጉሜ 2 ቀን 2014 ዓ.ም በፃፈው ድብዳቤ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ዞን እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያዎች የተማሪ መመዝገቢያ ክፍያ እንዲያቆሙ አሳስቧል።

ትምህርት ቢሮው የተማሪ ምዝገባ እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ያለው የዞኖች አፈፃፀም መገምገሙን ገልፆ “በግምገማው የተለየው ጉዳይ የዞኖች አፈፃፀም ዝቅተኛ መሆኑ ነው” ሲል አስረድቷል።

ቤሮው አክሎም ለምዝገባው ዘቅተኛ አፈፃፀም መመዝገብ የተለያዩ ምክንያቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቅሶ “ከበርካታ ወላጆች እየቀረበ ካለው ቅሬታዎች ወስጥ የተማሪ መመዝገቢያ ክፍያ እየተጠየቀ በመሆኑ በርካታ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት መጥተው እየተመዘገቡ እንዳልሆነ ተገንዝበናል” ብሏል።

ትምህርት ቢሮው በተጨማሪም ለተቀሱት ትምህርት መምሪያዎች “በመንግስት ትምህርት ቤቶች የተማሪ መመዝገቢያ ክፍያ ወጥ የሆነ ህጋዊ መመሪያ በቢሮው በኩል እስኪዘጋጅ ድረስ የተማሪ መመዝገቢያ ክፍያ ማስከፈል ባስቸኳይ እንዲቆም እንድታደርጉ” ሲል ያሳሰበ ሲሆን ከተማሪዎች ምዝገባ በኋል የወላጆች ድጋፍ ታሳቢ እንዲደረግ ብሏል።

ቢሮው ይህን ደብዳቤ ወጪ ከተደረገበት ዕለት ማለትም ከጳጉሜ 2 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከተሰጠው አቅጣጫ ውጪ የተላለፈ ማንኛውም የትምህርት መምሪያዎች ላይ “በአካባቢው ያለው የፀጥታ አካል የማስተካከያ እርምጃ ሊወስድ የሚችል መሆኑን እናሳስባለን” ሲል ጥብቅ ትዕዛዝ አሰተላልፏል። አስ

No comments

Sorry, the comment form is closed at this time.