አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22/2015 ዓ.ም፡- የአሜሪካ ሴኔት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር እንዲሆኑ በባይደን የቀረቡለትን ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋን ሹመት ማጽደቁ ተገለጸ። አምባሳደር ኤርቪን በባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሁነው የተመረጡት በያዝነው አመት ጥር ላይ መሆኑ ይታወቃል። ሹመታቸው በሴኔቱ የጸደቀላቸው አምባሳደር ኤርቪን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ምክትል ጸሓፊ ሁነው በማገልገል ላይ እንደነበሩ ተጠቁሟል።
አምባሳደር ኤርቪን የአሜሪካን መንግስት ወክለው በአፍሪካ በሱዳን እና በጊኒ መስራታቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።
በከፍተኛ የመንግስት ሀላፊነት ያካበተው ልምዱ፣ የተለያዩ ተቋማት ቡድኖችን በማቀናጀት የማሰራት ልምዱ እንዲሁም አሜሪካ በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ባላት ተልእኮ የነበረው የመሳተፍ እድል ኤርቪን ጆሴ ማሲንጋን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር እንዲሆኑ ተመራጭ አድርጓቸዋል ሲል ሹመታቸውን አስመልክቶ በወቅቱ የወጣው መግለጫ አትቷል።
አምባሳደር ኤርቪን በየካቲት 2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ የኤሜሪካን አምባሳደር ሁነው ተሹመው የነበሩትን እና አንድ አመት እንኳን ሳያገለግሉ ከተሰናበቱትን ጌታ ፓሲን በኋላ አሜሪካ የሾመችው የመጀመሪያ አምባሳደር መሆናቸው ተገልጿል። አስ