አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17/2015 ዓ.ም፡- ሩሲያ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአራት የአፈሪካ ሀገራት የ10 ሚሊየን ዶላር እርዳታ በአለም የምግብ ፕሮግራም በኩል እንደምትልክ አስታወቀች። ቡርኪናፋሶ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ኢትዮጰያ እያንዳንዳቸው ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊየን ዶላር እንደሚደርሳቸው በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር የፌስቡክ ገጹ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
የሩሲያ መንግስት በለገሰው ገንዘብ ሀገራቱ በሩሲያ ከሚገኙ ኩባንያዎች እርዳታውን እንዲገዙ እንደሚደረገ መግለጫው አመላክቷል። ለአራቱ የአፍሪካ ሀገራት የተደረገው የሩሲያ ልገሳ በአህጉሩ ያላትን ቦታ ያሳያል ሲል መግለጫው ጠቁሟል።